1ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር።
2አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን።
3ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።
4እርሱ የወረሰው ስም ከሰማቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ከመላእክትም የበለጠ ሆኖአል።
5ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ደግሞስ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ለማን ነው?
6የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል።
7ስለ መላእክቱ ግን፣"መላዕክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል" ይላል።
8ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው።
9ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” ብሏል።
10እንዲሁም፣ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ምድርን ፈጠርህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።
11እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ። ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
12እንደ መጎናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።
13በየትኛውም ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ከመላእክቱ ለአንዱ፣ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው?
14ታድያ፣ መላእክት ሁሉ እኔን እንዲያመልኩና ድነት የሚወርሱትን ለመርዳት ተተላኩ መንፈሶች አይደሉምን?