1የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤
2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ ‘ሰው’ ብሎ ጠራቸው።
3አዳም ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፣ ስሙንም ‘ሤት’ ብሎ ጠራው።
4አዳም ሤትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤
5930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
6ሤት ዕድሜው 105 ሲሆን ሄኖስን ወለደ።
7ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት 807 ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
8ሤት 912 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
9ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ።
10ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
11ሄኖስ 905 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
12ቃይናን 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ።
13ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
14ቃይናን 910 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
15መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ።
16መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
17መላልኤል 895 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
18ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሄሮክን ወለደ።
19ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
20ያሬድ 962 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
21ሄኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ።
22ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
23ሄኖክ 365 ዓመታት ኖረ።
24ሄኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ኖረ፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።
25ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜሕን ወለደ።
26ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ 782 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
27ማቱሳላ 969 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
28ላሜሕ 182 ዓመት ሲሆነው አንድ ወንድ ልጅ ወለደ።
29“ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል ስሙን ‘ኖህ’ ብሎ ጠራው።
30ላሜሕ ኖህን ከወለደ በኋላ 595 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
31ላሜሕ 777 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
32ኖህ 500 ዓመታት ሲሆነው ሴም፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።