1ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖንም ሹማምንት አንዱ የነበረውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጴጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።
2እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለነበረ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።
3አሳዳሪው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፣
4ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፣ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኃፊነት ሰጠው።
5ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብፅዊውን ቤት ባረከ፣ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
6ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፣ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ-መልካም ነበር፤
7ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስላፈቀረችው፣ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው።
8እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላልው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።
9በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኃላፊነት ያለው ማንም የለም፣ ከአንቺ በቀር በእኔ ቁጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እፈጽማለሁ?”
10ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርሷ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
11አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም፤
12እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ፣ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ።
13እርሷም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፣
14አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፣ “እነሆ፣ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደኝ ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ።
15ዕርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
16የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቆየችው።
17በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፤ “አንተ ወደዚህ የመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር።
18ነገር ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽሁ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
19“የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቆጣ።
20ዮሴፍንም ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደታሠሩበት እስር ቤት አስገባው።
21እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅሩን ዐሳየው፣ በእስር ቤት አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።
22ስለዚህ የእስር ቤቱ አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤት ላለውም ነገር ሁሉ ኃላፊ ሆነ።
23እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤት አዛዥ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ዐሳብ አልነበረበትም።