መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 36

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤
2ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣
3እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ።
4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት።
5እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው።
6ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።
7ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።
8ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
9በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
10የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
11የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤
12የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
13የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።
14የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤
15ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ
16ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።
17የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ።
18የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
19እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
20በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
21ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
22የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።
23የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤
24የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው።
25የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤
26የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤
27የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
28የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።
29የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣
30ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
31ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦
32የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
33ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።
34የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ።
35ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።
36ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
37ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።
38ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ።
39የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች።
40ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣
41አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣
42ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
43መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።