1በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
2በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ "ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤
3እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤
4ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።
5አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው።
6ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤
7በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ "ምንህናት" ብለው በጠየቁት ጊዜ "እኅቴ ናት" አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
8ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ።
9ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ "ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ "እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። እርሱም "ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው" ብሎ መለሰ።
10አቢሜሌክ "ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤"
11ቀጥሎም አቢሜሌክ "ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል"የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ።
12ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤
13ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
14ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።
15ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
16በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን "ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ" አለው።
17በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ።
18አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው።
19የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤
20የገራር እረኞች ግን "ይህ ውሃ የእኛ ነው" በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን "ዔሤቅ" ብሎ ሰየመው።
21የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ "ስጥና" ብሎ ሰየመው።
22ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ "እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት" ብሎ ሰየመው።
23ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤
24በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ" አለው።
25ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ።
26አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤
27ስለዚህ ይስሐቅ "ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?" አላቸው።
28እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣
29በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።"
30ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ።
31በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።
32ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ "ውሃ አገኘን" ብለውም አበሠሩት።
33እርሱም የውሃን ጉድጓድ "ሳቤህ"ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ "ቤርሳቤህ" እየተባለ ይጠራል።
34ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ።
35ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።