1አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤
2እርስዋም ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ መዳንን፣ ምድያምን፣ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት።
3ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የዳደንም ዝርያዎች አሹራውያን፣ ሌጡሻውያንና ሌአማውያን ናቸው።
4የምድያም ልጆች ዔፋ፣ ዔፈር፣ ሐኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚሁ ሁሉ የቁጠራ ዝርያዎች ናቸው።
5አብርሃም ያለው ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤
6ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።
7የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤
8በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤
9ልጆቹ ይሰሐቅና እስማኤል ማክጴላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊ በጶሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው።
10እነሱም አብርሃም ከሒታዊያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ።
11አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅ "ብኤርላሐይሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ" ተብሎ በመጠራት ኩሬ አጠገብ ይኖር ነበር።
12የሣራ አገልጋይ ግብፃዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን እስማኤል፤
13ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፣ ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሣም፣
14ሚሽማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣
15ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊሽና ቄድማ ናቸው።
16እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለአሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል።
17እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ።
18የእስማኤል ዝርያዎች ከግብፅ በስተምጅራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር። የኖሩበትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዝርያዎች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
19የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።
20ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሞኖሩ ሶሪያውያን ነበሩ።
21ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤
22የተፀነሱትም መንትያዎች ስለነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋ ነበር፤ እርስዋም "ይህን ዐይነት በገር ለምን ደረሰብኝ?" በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።
23እግዚአብሔርም ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ታናሹ አገልጋይ ይሆናል" አላት።
24የመውለጃዋም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።
25የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱ ጠጉራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ።
26ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተገረዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ስልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
27ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወደ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር።
28ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ምክንያቱም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ነበር።ርብቃ ግን ያዕቆብን ትንን ነበር።
29ለዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤
30ስለዚህም ያዕቆብ "ከዚህ ከቀይ ወጥ ሰጠኝ" አለው። ኤዶም የተባለውም ነዚሁ ምክንያት ነበር።
31ያዕቆብም "በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ" አለው።
32ዔሳውም "እኔ በረሀብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኩርና ምን ያደርግልኛል?" አለው።
33ያዕቆብም "እንግዲያውስ ብኩርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ" አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።
34ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኩርናውን በመናቅ አቃለላት።