መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም «አብርሃም»ብሎ ጠራው፤ «እነሆ አለሁኝ» ብሎ መለሰ።
2እግዚአብሔርም «የምትወደውን አንድ ልጅህን ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ። እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ» አለው፤
3አብርሃም በማለዳ ተነስቶ ለመስዋዕት የሚሆን እንጨት ቆረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅን ና ሁለት ወጣት ሰዎችን ይዞ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ።
4በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ።
5ከዚህ በኃላ አብርሃም የርሱን ወጣቶች «እናንተ ከአህያው ጋር በዚህ ቆዩ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ከሰገድን በኃላ እንመለሳለን፤
6አብርሃምም የሚቃጠለውን መስዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንስቶ ለልጁ ለይስአቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢላዋውንና እሳቱን ያዘ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
7ይስሐቅ አብርሃምን «አባባ» አለው፤ እርሱም «እነሆ አለሁ ልጄ» አለው፤ ይስሐቅም «እነሆ እሳትና እንጨት ይዘናል ታዲያ ለመስዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?» በማለት አብርሃምን ጠየቀው።
8አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
9እግዚአብሔር ነገረው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሰዊያ ሰርቶ እንጨቱን ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሰዊያው ላይ አጋደመው።
10ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንስቶ እጁን ዘረጋ።
11ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ «አብርሃም! አብርሃም!» ብሎ ጠራው። እርሱም «እነሆኝ አለሁኝ» አለ።
12እርሱም «በልጁ ላይ እጅህን አትጫንበት፣ ምንም ዓይነት ጉዳትም አታድርስበት፣ እነሆ እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቻለሁ፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት አልተቆጠብህም» አለው።
13አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው።
14አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።
15የእግዚአብሔር መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ከሰማይ ጠራውና፤
16እንዲህ አለው፤ «እግዚአብሔር ብዙ በረከት እንድምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ» ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቆጠብህ፤
17እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባህር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዝርያዎችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው፤ ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።
18ትዕዛዜን ስለ ፈጸምህ የዓለም ህዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ»፤
19ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ ወጣቶችሁ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።
20ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው «ሚልካ ልጆችን ለወንድምህ ለናኮር ወልዳለች፤
21እነርሱም የመጀመሪያው ልጅ ዑፅ ወንድሙም ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፤
22ኬሰድ፣ ሐዞ፣ ፊልዳሽ፤ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።
23በቱኤል ርብቃን ወለደ። ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለንኮር ወለደችለት፤
24ረኡማ የተባለች የናኮር ቁባት ደግሞ ጤባሕን፣ ገሐምን፣ ተሐሽና ማዕካን ወለደችለት።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።