መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 23

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው።
2በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም።
3ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤
4«እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።»
5የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤
6«ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።»
7አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ።
8የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤
9በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።»
10ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
11«አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።»
12አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ።
13የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ
14ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
15«ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር»
16አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት።
17በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤
18እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።
19ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ።
20እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።