1ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤
2ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
3አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት።
4ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው።
5ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር።
6ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች።
7ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች።
8ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ።
9ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች።
10ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው።
11እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው
12እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ።
13የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው
14አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር።
15በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው።
16እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር።
17እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ።
18ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
19በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው።
20ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር።
21በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።
22በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
23እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው።
24አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ።
25አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤
26አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው።
27ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ።
28በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤
29አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው?» አለው።
30አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤
31ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤
32ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ
33ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤
34አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።