1ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት።
2እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።
3አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ።
4ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ።
5ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።
6ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት።
7ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው።
8አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።
9እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ።
10እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር።
11በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር።
12ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች።
13ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው?
14ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።"
15ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት።
16ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ።
17በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን?
18አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ።
19ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።"
20ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤
21ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።"
22ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር።
23አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?
24ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን?
25ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን?
26ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።"
27አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤
28ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ።
29አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ።
30አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ።
31አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ።
32በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ።
33ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።