1ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።
2እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት።
3ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ።
4ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት።
5ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት።
6ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ።
7እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ።
8ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።"
9እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር።
10ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ።
11ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር።
12ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ።
13ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።"
14ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው።
15ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት።
16ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው።
17ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።"
18ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣
19እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል።
20ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።"
21እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም።
22አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች።
23ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር።
24ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ።
25እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ።
26ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች።
27አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ።
28ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር።
29እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው።
30ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ።
31ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም።
32ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።"
33ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም።
34በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።"
35ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
36ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ።
37ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ።
38ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።