1አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ።
2በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።"
3አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤
4"እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።
5ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ።
6እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ።
7በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ።
8ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።"
9ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ።
10በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
11እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።
12በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል።
13ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል።
14ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።"
15እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት።
16እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ።
17በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?"
18አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ።
19እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ።
20እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ።
21ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።"
22ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ።
23በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው።
24አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር።
25ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር።
26በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ።
27ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።