1የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት።
2አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ።
3የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር።
4አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች።
5በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው።
6አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች።
7የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር።
8መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው።
9የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት።
10ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት።
11የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
12እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።"
13እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር።
14ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው።
15አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው።
16አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።