መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።”
2አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው?” አለ።
3በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ።
4በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።”
5ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።”
6አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።
7እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።”
8አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ።
9በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው።
10እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም።
11አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው።
12ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት።
13በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ።
14እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ።
15አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ።
16በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።”
17ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ።
18በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
19የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣
20የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣
21የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።