መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣
2በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ።
3እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ።
4እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ።
5በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣
6የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው።
7ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።
8ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ።
9እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው።
10በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ።
11አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ።
12በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ።
13ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር።
14ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው።
15አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።
16ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ።
17አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
18የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር።
19አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣ “ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ።
20ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።” አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።
21የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።
22አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣
23ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ።
24አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።