መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ።
2በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር።
3ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ።
4ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ።
5ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት።
6ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም።
7ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።
8አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን።
9ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።
10ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
11ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ።
12አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ።
13የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ።
14ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት።
15ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።
16ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም።
17እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።”
18ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።