1በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር።
2ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።
3እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ።
4ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ።
5የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ።
6ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም።
7ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ።
8ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ።
9በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው።
10የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ።
11አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
12አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤
13ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
14ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤
15ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
16ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤
17ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
18ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤
19ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
20ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤
21ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
22ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤
23ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
24ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
25ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ።
26ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።
27የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ።
28ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ።
29አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር።
30ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች።
31ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።
32ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።