መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው። ከጥፋት ውሃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
2የያፌት ልጆች፦ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕና ቴራስ ነበሩ።
3የጋሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋትና ቴርጋማ ነበሩ።
4የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲምና ሮዳኢ ነበሩ።
5ከእነዚህም በየነገዳቸው በየጎሳቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
6የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥና ከነዓን ነበሩ።
7የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰበቀታ ነበሩ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ድዳን ነበሩ።
8ኩሽ በምድር ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረው የናምሩድ አባት ነበር።
9እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ ነበር። ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።
10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች በሰናዖር ምድር የነበሩት፡- ባቢሎን፣ አሬክ፣ አርካድና ካልኔ ነበሩ።
11ከዚያም ወደ አሦር ምድር ሄደና ነነዌን፣ ርሆቦትን፣ ካላሕን
12እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል የነበረውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ።
13ምጽራይም የሎዳማውያን፣የዐናሚማውያን፣ የላህሚማውያን፣ የነፍታሌማውያን፣
14የፈተሩሲማውያንና ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካስሎሂማውያንና የቀፍቶርማውያን አባት ነበር።
15የከነዓንም የበኩር ልጅ ሲዶን ተከታዩም ሔት ይባሉ ነበር።
16ሌሎቹም የከነዓን ዝርያዎች ኢያቡሳውያን፣ አሞራውያን፣ ጌርጌሳውያን፣
17ኤውያውያንን፣ ዓርቃውያን፣ ሲናውያን፣
18ኤርዋዳውያን፣ አርዋዳውያን፣ ደማራውያን፣ ሐማታውያን የሚባሉ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጎሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ።
19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል ገሞራን አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
20እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ነበሩ።
21ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነበር።
22የሴም ልጆች ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ነበሩ።
23የአራም ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ነበሩ።
24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ።
25ዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
26ዮቅጣንም የአልሞዳድ፣ የሼሌፍ፥ የሐጸርማዌት፣ የዮራሕ፣
27የዐዶራም፣ የኢዛል፣ የዲቅላ፣
28የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣
29የኦፊር፣ የሐዊላና የዮባብ አባት ነበር። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዝርያዎች ነበሩ።
30መኖርያ ስፍራቸውም በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ስፋር ይደርስ ነበር።
31እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ነበሩ።
32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጎሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።