መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ገላቲያ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ።
2የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር።
3ግሪካዊ የሆነው ሲላስ እንኳ እንዲገረዝ አልተገደደም።
4ይህ ጉዳይ የተንሳው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት ለመሰለል ሾልከው በገቡ ውሸተኞች ወንድሞች ምክንያት ነበር።
5የህግ ባሪያዎች ሊያደርጉን ይመኙ ነበር። ነገር ግን ለእናንተ ወንጌሉ ሳይለወጥ ይቆይላችሁ ዘንድ ለአንድ ሰዓት እንኳ ለሀሳባቸው አልተገዛንም።
6ነገር ግን ሌሎች መሪዎች ናቸው ያልዋቸው ምንም አስተዋፅኦ አላደርጉልኝም። ማንም ይሁኑ ለእኔ ትርጉም አልነበረውም። ሆኖም ግን ልክ ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተሰጠው ሁሉ
7እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተቀበልኩ አዩ፥
8ምክንያቱም ለተገረዙት ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ በጴጥሮስ የሰራ እግዚአብሔር ላልተገረዙት ሃዋሪያ እሆን ዘንድ በእኔም ስለሚስራ ነው።
9እንደመሪዎች የሚታወቁት ያዕቆብ፥ኬፋና ዮሀንስ በእኔ ላይ ያለውን ፀጋ ባዩ ጊዜ እኛ ወደ አህዛብ እነርሱ ደግሞ ወደተገረዙት ይሄዱ ዘንድ የማህበራቸውም ተካፋዮች እንድንሆን ሙሉ መብት ሰጡን።
10እኔ ለማድረግ የምናፍቀውን ድሆችን እንድናስብም አሳሰቡን።
11ከዚያም ኬፋ ወደ አንፆኪያ በመጣ ጊዜ ሥራው ትክክል ስላልነበረ ፊት ለፊት ተቃወምኩት።
12ምክንያቱም ከያዕቆብ ዘንድ ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት ኬፋ ከአህዛብ ጋር ይበላ ነበር። ሰዎቹ በመጡ ጊዜ ግን እነኚህን የተገረዙ ሰዎች ፈርቶ ከአህዛብ ጋር መብላቱን አቆመ እንዲያውም ተለያቸው።
13በርናባስ እንኳ በግብዝነታቸው እስኪሳብ ድረስ ሌሎቹም አይሁድ በኬፋ ግብዝነት ተካፋዮች ነበሩ።
14ወንጌልን በሚፃረር መንገድ መሄዳቸውን ባየሁ ጊዜ ኬፋን በሁሉም ፊት «አንተ አይሁዳዊ ሆንህ በአህዛብ ስርአት የምትኖር ከሆነ አህዛብ በአይሁድ ስርአት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋልህ?» አልኩት።
15እኛ«አህዛብ ኃጢአተኞች» ያልሆንን ነገር ግን በትውልድ አይሁዳዊ የሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንጂ ማንም ህግን በመፈፀም እንደምይፀድቅ እናውቃለን።
16በህግ ሥራ ማንም ሊፀድቅ ስለማይችል በህግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት እንፀድቅ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እምነት ተጠርተናል።
17ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲያፀድቀን እየፈለግን ሳለ ራሳችንን ኃጢአተኞች ሆነን እናገኛለን፥
18ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ሆነ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም።
19ምክንያቱም አውልቄ የጣልኩትን ህግን የመፈፀም ትምክህት እንደገና ብገነባ ራሴን ህግ ተላላፊ ሆኜ አገኘዋለሁ። በህግ በኩል ለህግ ሞቼአለሁ።
20ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
21የእግዚአብሔርን ፀጋ አላቃልልም፥ ህግን በመጠበቅ ፅድቅ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ መሞቱ ከንቱ በሆነ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።