መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ገላቲያ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰው በኩል ወይም ከሰው ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞም እርሱን ከሞት ባስነሳው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆንኩት ጳውሎስ
2አብረውኝ ካሉ ወንድሞች ጋር በገላትያ ለምትገኙ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ
3ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ
4ይሁን፣እርሱ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከአሁኑ ክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ እራሱን ስለ ኃጢአታችን ሰጥቶአልና
5ለእርሱ ከዘላለም እስከዘላለም ክብር ይሁን። አሜን!
6ወደሌላ ወንጌል በዚህ ፍጥነት በመዞራችሁ እጅግ ተገርሜአለሁ። በክርስቶስ ጸጋ ከተጠራችሁ ከእርሱ ፊታችሁን ማዞራችሁ አስገርሞኛል።
7ሌላ ወንጌል የለም፣ ነገር ግን የሚያውኩዋችሁና የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።
8ነገር ግን እኛም ሆንን የሰማይ መልአክ አስቀድመን ከሰበክንላችሁ ሌላ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
9አስቀድመን እንዳልን እንደገና እላለሁ «ማንም ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገም ይሁን»
10ለመሆኑ እኔ የምጥረው ከሰው ወይስ ከእግዚአብሔር ይሁንታን ለማግኘት ነው? ጥረቴ ሰውን ለማስደሰት ነው? እስከአሁን ድረስ ሰውን ለማስደሰት እየጣርኩ ከሆነ እውነት እኔ የክርስቶስ አገልጋይ አይደለሁም።
11ወንድሞች ሆይ የሰብኩላችሁ ወንጌል ከሰው እንዳልሆን እንድታውቁ እፈልጋለሁ።
12ከጌታ ከኢየሱስ ከተሰጠኝ መገለጥ እንጂ ከሰው አልተቀበልኩትም ከሰውም አልተማርኩትም።
13የይሁዲ እምነት ተከታይ በነበርኩበት በቀድሞው ህይወቴ ወቅት እንዴት ቤተክርስቲያንን በአመፅ አሳድድና አጠፋ እንደነበረ ስለእኔ ሰምታችኋል።
14በይሁዲነት ከአብዛኛዎቹ አብረውኝ ከነበሩ አይሁዶች እየላቅሁ ነበር። ለአባቶቼም ወግ ከመጠን ያለፈ ቀናኢ ነበርኩ።
15ነገር ግን እግዚአብሔር ገና በማህጸን ሳለሁ ሊመርጥኝ ወደደ፣
16በአረማውያን መካከል አውጀው ዘንድ ልጁን በእኔ ለመግለፅ በጸጋው ጠራኝ። በጠራኝ ጊዜ ወዲያውኑ ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም
17፣ከእኔ አስቀድመው ሃዋሪያት የሆኑት ወደሚገኙበት ወደ ኢየሩሳሌምም አልሄድኩም። ነገር ግን ወደ አረቢያ በኋላም ደግሞ ወደ መቄዶኒያ ተመለስኩ።
18ከዚያም ከሶስት አመት በኋላ ኬፋን ለመጠየቅ ወደኢየሩሳሌም ሄጄ ከእርሱ ጋር አስራአምስት ቀናት ቆየሁ።
19ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በስተቀር ሌሎች ሃዋሪያትን አላገኘሁም።
20በምፅፍላችሁ በእነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳልዋሸሁ እወቁ።
21ቀጥሎም ወደ ሶሪያና ኪልቂያ አውራጃዎች ሄድኩኝ።
22እስከዚያን ጊዜ ድረስ በይሁዳ ላሉት አብያተክርስቲያናት በአካል አልታወቅም ነበር፣
23ነገር ግን «ያ ቀድሞ ያሳድደን የነበረው ሰው አሁን ሊያጠፋው ሲጥር የነበረውን እምነት እየሰበከ ነው» የሚል ወሬ ብቻ ይሰሙ ነበር፣
24ስለ እኔም እግዚአብሔርንም ያከብሩ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።