መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ገላቲያ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ የገላቲያ ሰዎች ማነው በክፉ ዓይኑ ያያችሁ፥ ክርስቶስ እንደተሰቀል ሆኖ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረምን?
2ይህን ብቻ ከእናንተ ማወቅ እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት በህግ ሥራ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ?
3ይህን ያህል ሞኞች ናችሁ እንዴ፥ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ትጨርሳላችሁ?
4በእርግጥ ይህ ከንቱ ከተባለ ያን ሁሉ መከራ የተቀብላችሁት በከንቱ ነውን?
5መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁና በመካከላችሁ ኃይለኛ ነገርን ያደረገው እርሱ ይህን ያደረገው በህግ ሥራ ነው ወይስ ከእምነት በሆነ እምነታችሁ ነው?
6ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት»
7የሚያምኑ ሁሉ የአብርሀም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ።
8ቅዱሳት መፅሀፍት እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚያፀድቅ አስቀድመው አመልክተዋል። ወንጌል «አህዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» ተብሎ በመጀመሪያ ለአብርሀም ተሰብኳል።
9ስለዚህም የሚያምኑ እምነት ከነበረው ከአብርሀም ጋር የተባረኩ ናቸው።
10«ህግን ሁሉ ይፈፅም ዘንድ ለህግ የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ነው» ተብሎ ተፅፎአልና በህግ ስራ የሚታመን ሁሉ በእርግማን ስር ነው።
11«ጻድቅ በእምነት ይኖራልና» እግዚአብሔር ማንንም በህግ እንደማያጸድቅ ግልጽ ነው።
12ህግ ከእምነት የመነጨ አይደለም፥ ይልቁኑም «በህግ ውስጥ ያሉትን እነዚያን ነገሮች የሚያደርግ በህግ ይኖራል»
13«በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።
14የዚህ ተግባር ዓላማ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ በእምነት እንቀበል ዘንድ በአብርሀም ላይ የነበረው በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በአህዛብም ላይ እንዲሆን ነው።
15የምናገረው በሰው ቋንቋ ነው። ልክ በሰዎች መካከል እንደተደረገ ውል ማንም ከዚህ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር አይችልም።
16እንግዲህ ተስፋዎቹ የተነገሩት ለአብርሀምና ለዘሩ ነው። ብዙ ሰዎችን እንደሚያመለክት «ለዘሮቹ» አላለም። ነገር ግን አንድ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ«ለዘሩ» ብሎ ይናገራል። ያም ለዘሩ የተባለለት ክርስቶስ ነው።
17እንግዲህ እንዲህ ልበል። አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠው ቃል ኪዳን ተስፋ ከ430 ዓመት በኋላ በተሰጠ ህግ አልተሻረም።
18ምክንያቱም ውርሱ በህግ የመጣ ቢሆን ኖሮ በተስፋ በኩል ባልመጣ ነበር፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም በተስፋ አማካኝነት ርስትን እንዲያው ሰጠው።
19ታዲያ ህግ ለምን አስፈለገ? የአብርሃም ዘር ተስፋ ወደተሰጣቸው እስኪመጣ ድረስ በመተላለፍ ምክንያት ህግ ተሰጠ፤ ህጉ በመካከለኛ አማካኝነት በመላዕክት አማካኝነት ተግባራዊ ሆኗል።
20መካከለኛ ሲል ከአንድ ሰው በላይ እንደሆነ ያመለክታል፥ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
21ታዲያ ህግ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይቃረናል ማለት ነው? በፍጹም አይደለም። ህይወትን ሊሰጥ የሚችል ህግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት ጽድቅ በህግ በኩል ይመጣ ነበር።
22ነገር ግን ይልቁኑ መጽሀፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች እስርኛ አድርጓል። ስለዚህም እኛን በክርስቶስ ኢየሱስ ለማዳን እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ለሚያምኑ ተሰጠ።
23ነገር ግን በክርስቶስ ማመን ከመምጣቱ በፊት እምነት እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በህግ ታስረንና ታግደን ነበር።
24ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ ህግ ወደ ክርስቶስ ዘመን የሚያደርሰን ሞግዚት ሆነ።
25አሁን እምነት ስለመጣ ከዚህ በኋላ በሞግዚት ሥር አይደለንም።
26ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።
27በክርስቶስ ስም የተጠምቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።
28ሁላችሁ በክርስቶስ አንድ ስለሆናችሁ በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች፥ በባሪያና ነጻ በሆነ፥በሴትና በወንድ መካከል ልዩነት የለም።
29እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።