መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕዝራ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በትውልዱ የሠራያ፥ ዓዛርያስ፥ ኬልቅያስ፥
2ሰሎም፥ ሳዶቅ፥ አኪጦብ፥
3አማርያ፥ ዓዛርያስ፥ መራዮት፥
4ዘራአያ፥ ኦዚ፥ ቡቂ፥
5አቢሱ፥ ፊንሐስ፥ አልዓዛር ከዚያም የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ የሆነው ዕዝራ -
6ዕዝራ ባቢሎንን ለቆ ወጣ። እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ በሚገባ የተካነ ጸሐፊ ነበር። የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ሰጠው።
7ደግሞም በንጉሥ አርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት አንዳንድ የእስራኤል ተወላጆችና ካህናቱ፥ ሌዋውያን፥ የቤተ መቅደስ መዘምራን፥ በር ጠባቂዎችና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።
8እርሱም በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም ደረሰ።
9በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባቢሎንን ለቀቀ። መልካሚቱ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ ኢየሩሳሌም የደረሰው በአምስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ነበር።
10ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ለማጥናት፥ ለመተግበርና ሥርዓትና ትዕዛዙን ለማስተማር ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።
11ንጉሡ አርጤክስስ ለካህኑና እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ትዕዛዝና ሥርዓት ጸሐፊና ለሆነው ለዕዝራ የሰጠው ትዕዛዝ ይህ ነበር፤
12ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፥ የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፤
13በመንግሥቴ ውስጥ እስራኤላዊ የሆነ ማንም ቢሆን ከካህናቶቻቸውና ከሌዋውያኖቻቸው ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚወዱ ካንተ ጋር እንዲሄዱ አዝዣለሁ።
14ይሁዳና ኢየሩሳሌምን በሚመለከት በምታውቀው በእግዚአብሔር ሕግ እንድትመረምር፥
15ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ እንድትወስድ እኔ ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቼ ልከንሃል።
16ሕዝቡና ካህናቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ካቀረቡት በተጨማሪ ባቢሎናዊያን በሙሉ የሰጡትን ወርቅና ብር ሁሉ በነጻ ስጥ።
17ስለዚህ በሬዎችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን፥ ስንዴና የመጠጥ ቁርባኑን በርከት አድርገህ ግዛ። በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት መሠዊያ ላይ ሠዋቸው።
18በቀረው ብርና ወርቅ አምላክህን ለማስደሰት አንተና ወንድሞችህ መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አድርጉበት።
19በፈቃደኝነት የተሰጡህን ዕቃዎች በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት ለአገልግሎት እንዲሆን በፊቱ አስቀምጥ።
20ለአምላክህ ቤት ያስፈልጋል ብለህ ለምትጠይቀው ለየትኛውም ተጨማሪ ወጪ ገንዘቡን ከግምጃ ቤቴ ውሰድ።
21እኔ ንጉሥ አርጤክስስ በወንዙ ማዶ ላላችሁት የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ፥ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ማናቸውንም ነገር በዛ አድርጋችሁ እንድትሰጡት አዝዣለሁ፥
22እስከ አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አንድ መቶ ቆሮስ ስንዴ፥ አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ወይንና አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ደግሞም ያለ መጠን የሆነ ጨው ስጡአቸው።
23ከሰማይ አምላክ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ለቤቱ በትጋት አድርጉት። በእኔና በልጆቼ መንግሥት ላይ ቁጣው ለምን ይምጣብን?
24በካህናቱ፥ በሌዋውያኑ፥ በሙዚቀኞቹ፥ በበር ጠባቂዎቹ ወይም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት በተመደቡት ሰዎችና የዚህ አምላክ ቤት አገልጋዮች በሆኑት ላይ ምንም ዓይነት እጅ መንሻም ሆነ ቀረጥ እንዳይጥሉ ስለ እናንተ እናስታውቃቸዋለን።
25አንተም ዕዝራ፥ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብ መሠረት በወንዙ ማዶ ያሉትን ሰዎች ሁሉ እና የአምላክህን ሕግ የሚያውቀውን ማንኛውንም ሰው እንዲያገለግሏቸው ፈራጆችንና አስተዋዮችን ሰዎች መሾም አለብህ። አንተ ደግሞ እነዚያን ሕጉን የማያውቁትን ሰዎች አስተምራቸው።
26የእግዚአብሔርን ሕግ ወይም የንጉሡን ሕግ ሙሉ በሙሉ የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው በሞት፥ በስደት፥ ንብረቱን በመውረስ ወይም በእስራት ቅጣው።"
27ዕዝራም አለ፥ "በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለማስዋብ ይህንን ሁሉ በንጉሡ ልብ ያኖረና ደግሞም በንጉሡ፥
28በአማካሪዎቹና በኃያላን አለቆቹ ሁሉ ፊት የቃል ኪዳን ታማኝነቱን በእኔ ላይ ያበዛ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁኝ፥ ከእኔ ጋር እንዲሄዱም የእስራኤልን አለቆች ሰበሰብሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።