መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕዝራ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ነቢዩ ሐጌና የአዶ ልጅ ንቢዩ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩ።
2የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ካደፋፈሯቸው ነቢያት ጋር በመሆን በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመሩ።
3ከወንዙ ማዶ ያለው አውራጃ አስተዳዳሪ ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው መጥተው፥ "በማን ትዕዛዝ ነው ይህንን ቤት የምትሠሩትና የቅጥሮቹን ጥገና እየጨረሳችሁ ያላችሁት?" አሏቸው።
4ደግሞም፥ "ይህን ሕንፃ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ማን ነው?" አሏቸው።
5ነገር ግን የእግዚአብሔር ዓይን በአይሁድ አለቆች ላይ ነበር፥ ጠላቶቻቸውም አላስቆሟቸውም። እነርሱም በዚህ ጉዳይ ለንጉሡ ደብዳቤ ለመጻፍና ትዕዛዝ እስኪመጣላቸው ይጠብቁ ነበር።
6ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው የሆኑት አለቆች ለንጉሡ ለዳርዮስ የጻፉት ደብዳቤ ይህ ነበር፤
7እንዲህ ሲሉ ለንጉሡ ዳርዮስ ጻፉለት፤ "ሙሉ ሰላም ለአንተ ይሁን።
8ወደ ይሁዳ ወደ ታላቁ አምላክ ቤት ሄደን እንደነበረ ንጉሡ ይወቅ። እርሱም በታላላቅ ድንጋዮች እየተሠራና በቅጥሮቹም መሐል እንጨቶችን እያስገቡበት ነው። ሥራው በትጋት እየተሠራና በእጆቻቸው ላይ በመከናወን ላይ ይገኛል።
9አለቆቹንም፥ "ይህንን ቤትና ቅጥሮቹን እንድትሠሩ የፈቀደላችሁ ማነው?" ብለን ጠየቅናቸው።
10ደግሞም የሚመሯቸውን ሰዎች የእያንዳንዳቸውን ስም ታውቅ ዘንድ ስሞቻቸውን እንዲነግሩን ጠየቅናቸው።
11እነርሱም መልሰው፤ "እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙ ዓመታት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ የሠራውንና የጨረሰውን ይህንን ቤት በማደስ ላይ ነን።
12ይሁንና አባቶቻችን የሰማይን አምላክ ባስቆጡት ጊዜ ይህንን ቤት ባፈረሰውና ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
13ሆኖም ቂሮስ በባቢሎን ላይ በነገሠ ጊዜ በመጀመሪያው ዓመት የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ትዕዛዝ ሰጠ።
14ደግሞም ንጉሥ ቂሮስ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በባቢሎን ወደሚገኘው መቅደስ ያመጣቸውን የእግዚአብሔር ቤት መገልገያ የሆኑትን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች መለሰ። አስተዳዳሪ እንዲሆን ለሾመው ለሰሳብሳር አስረከበው።
15እርሱንም፥ "እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ። ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው። በዚያም የእግዚአብሔር ቤት ይሠራ" አለው።
16ከዚያም ይህ ሰሳብሳር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመሠራት ላይ ነው፥ ይሁን እንጂ እስካሁን አላለቀም።
17አሁንም ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ ያዘዘው ትዕዛዝ በባቢሎን መዝገብ ቤት ይገኝ እንደሆን ይመርመር፤ ከዚያም ንጉሡ ውሳኔውን ይላክልን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።