መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም "ጠባቂዎች የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ወደ ከተማይቱ ይቅረቡ" ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ።
2እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች በሰሜን አቅጣጫ ካለው ከላይኛው በር በኩል መጡ፣ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
3የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄደ። በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።
4እግዚአብሔርም "በኢየሩሳሌም ከተማ መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት አድርግ" አለው።
5እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ "እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም! ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም
6ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ! ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ። ከመቅደሴም ጀምሩ!" አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
7እርሱም "ቀጥሉ! ቤቱን አርክሱ፥ አደባባዮቹንም በሬሳ" አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ላይ ጥቃት ፈጸሙ።
8ጥቃቱን እየፈጸሙ ሳሉ እኔ ብቻዬን እንደቀረሁ ሳይ በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?" ብዬ ጮኽሁ።
9እርሱም፦ "'እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም!' እያሉ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች ።
10እኔም ደግሞ ዓይኔ አትራራላቸውም አላዝንምም። ይልቁኑ መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ" አለኝ።
11እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው ተመልሶ መጣና "ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ" የሚል ሪፖርት አቀረበ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።