መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
2"አንተ የሰው ልጅ ሆይ -- ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር የሚለው እንዲህ ነው፣ 'መጨረሻ! በምድሪቱ አራቱም ማዕዘን መጨረሻ መጥቷል!
3ቁጣዬን ስለላኩባችሁ መጨረሻችሁ ቀርቧል፣ እኔም እንደመንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ በእናንተ ላይ እመልስባችኋለሁ።
4በርህራሄ አላያችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም፤ ነገር ግን መንግዳችሁን እመልስባችኋለሁ፣ ጥፋታችሁ በመካከላችሁ ይሆናል፥ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!
5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መዓት! በመዓት ላይ መዓት! እነሆ እየመጣ ነው!
6መጨረሻ በእርግጥ እየመጣ ነው፤ መጨረሻው ወደ እናንተ እየተራመደ ነው! እነሆ እየመጣ ነው!
7በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ ፍርድ እየመጣ ነው። ጊዜው ደርሷል፤ የጥፋት ቀን ቀርቧል፤ ተራሮች ከእንግዲህ ለደስታ አይሆኑም።
8በቅርቡ እንደ መንገዳችሁ በምፈረድባችሁ ጊዜና ክፋታችሁን በመለስኩባችሁ ጊዜ መዓቴን አፈስባችኋለሁ ቁጣዬም በላያችሁ ይሆናል።
9ዓይኔ አይራራላችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም። እንዳደርጋችሁብኝ አደርግባችኋለሁ፤ የምቀጣችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ ክፋታችሁም በመካከላችሁ ይሆናል።
10እነሆ ቀኑ እየደረሰ ነው። ጥፋት ወጥቷል። በትሩ በትዕቢት አበባ ፈክቷል።
11አመጽ ወደ ኃጢአት በትርነት አድጓል-- አንዳቸውም፣ ከህዝባቸውም ማንም፣ የትኛውም ሀብታቸው፣ የትኛው ጠቃሚ ነገራቸው አይተርፍም።
12ቀኑ እየመጣ ነው፤ ቀኑ እየቀረበ ነው። ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ስለሆነ ንብረት የገዛ አይደሰት፣ የሸጠም አይዘን!
13ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሻጭ የሸጠውን አያስመልስም፣ ራዕዩ ለመላው ህዝብ ነው። በኃጢአቱ የሚጸና አይበረታምና አይመለሱም።
14መለከት ነፉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጁ ነገር ግን ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ነውና ለጦርነት የከተተ አንድም የለም!
15በውጭ ሰይፍ በውስጥ ደግሞ ረሀብና ቸነፈር አለ። በእርሻ ቦታ ያሉ በስይፌ ይወድቃሉ፥ ረሀብና ቸነፈር ደግሞ በከተማ ያሉትን ይፈጃል።
16ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ተርፈው ወደ ተራሮች ይሄዳሉ። ሁሉም ስለኃጢአታቸው እያንዳንዱም ስለስንፍናው እንደ ደሸለቆ እርግብ ያለቅሳሉ።
17እጅ ሁሉ ይቀልጣል ጉልበትም ሁሉ እንደ ውሀ ይደክማል፣
18ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይከባቸዋል፤ ፊት ሁሉ በእፍረት ይሸፈናል ራስም ሁሉ ጠጉር አልባ ይሆናል።
19ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም
20የክብሩ ጌጦችንም በማንአለብኝነት ወስደው ክፋታቸውንና የፈጸሙትን አመጻ የሚያሳዩ የምንዝርና ምስሎችን አበጁ፣ ስለዚህ እኔ እነዚህን ምስሎች ርኩስ እድርጌባቸዋለሁ።
21በባዕድም እጅ ለንጥቂያ፥ በምድር ኃጢአተኞችም እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ እነርሱም ያረክሱአቸዋል።
22የተቀድሰውን ቦታዬን ባረከሱ ጊዜ ፊቴንም አዞርባቸዋለሁ፥ ወንበዴዎችም ይገቡባታል ያረክሱትማል።
23ምድሪቱ ደም ባመጣው ፍርድ፥ ከተማዪቱም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ።
24ስለዚህም ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፣ መቅደሶቻቸው ስለሚረክሱ የኃያላንንም ትዕቢት ወደ ፍጻሜ አመጣለሁ።
25ፍርሀት ይመጣል! ሰላምን ይሻሉ ነገር ግን ምንም ሰላም አይገኝም።
26ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ወሬም በወሬ ላይ ይመጣል! ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ ነገር ግን ከካህኑም ዘንድ ህግ፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።
27ንጉሡም ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝብ እጆቼ በፍርሀት ይንቀጥቀጣሉ። እንደ መንገዳቸውም መጠን ይህን አደርግባቸዋለሁ! እኔ እግዚአብሔር እንድሆንኩ እስኪያውቁ ድረስ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።