1የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ
2"የሰው ልጅ ሆይ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙርና ትንቢት ተናገር።
3እንዲህም በላቸው 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፣ ለኮረብቶች፣ ለሸንተረሮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፡ እነሆ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ ከፍታችሁን ሁሉ አጠፋለሁ።
4መሰዊያዎቻችሁ ባድማ ይሆናሉ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁም ይደመሰሳሉ የሞቱ ሰዎቻችሁን ሬሳዎች በጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ።
5የእስራኤልን ህዝብ ሬሳዎችን በጣዖቶቻችው ፊት አጋድማለሁ፣ አጥንቶቻችሁንም በመሰዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።
6መሰዊያዎቻችሁ የተጣሉና ባድማ እንዲሆኑ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ የተጣሉ የማምለኪያ ኮረብቶቻቸው ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፣ እንዳልነበሩም ሆነው ይጠፋሉ፤ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁ ይወገዳሉ ሥራቼሁ ሁሉ ተጠርጎ ይጠፋል።
7የሰዎች ሬሳ በመካከላችሁ ይወድቃል ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!
8ነገር ግን ቅሬታዎችን አስቀራለሁ፣ እናንተ በየአገሩ ስትበተኑ ከአህዛብ መካከል ከሰይፍ የሚያመልጡ ይኖራሉ።
9እነዚያ ያመለጡትም በምርኮ አገር ሆነው ከእኔ ዘወር ካለው አመንዝራ ልባቸውና ወደ ጣዖታቶቻቸው ከሚያየው አመንዝራ ዓይናቸው የተነሳ ምን ያህል እንዳዝንኩ ስለእኔ ያስባሉ። ባደረጉት ክፋትና ርኩሰት መጸጸታቸው ከፊታቸው ይነበባል።
10ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ይህን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ አስቀድሜ የተናገርኩት በዓላማ ነው።
11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ከፈጸሙት አስነዋሪ ተግባር የተነሳ የእስራኤል ህዝብ በሰይፍ፣ በረህብና በቸነፈር ይጠፋሉና በእጅህ እያጨበጭችብክ በእግርህም መሬቱን እየመታህ "ወዮ" እያልክ ጩህ!
12በሩቅ ያለው በቸነፈር በቅርብ ያለው በሰይፍ ይጠፋሉ። ከዚያ የተረፉት ደግሞ በርሀብ ያልቃሉ፤ በዚህ መንገድ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።
13በጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሰዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባሉ ተራሮቼ አናት ላይ፣ እንዲሁም በለመለመ ዛፍ ሁሉና በግዙፍ ዋርካ ስር- ለጣዖቶቻቸው በሚያጤኑበት ሥፍራ ሁሉ የተገደሉ ሰዎቻቸው ተጥለው ሲያዩ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ።
14በገዛ እጄ እመታችኋለሁ የሚኖሩብትን ስፍራ ሁሉ ከምድረ በዳ እስከ ዲብላህ ድረስ ምድሪቱን የተጣለችና ባድማ አደርጋታለሁ።"