1"ከዚያም የሰው ልጅ ሆይ ጎራዴን እንደጢም መላጫ ተጠቀመህ ራስህንም ጢምህንም ተላጨው፣ በመቀጠልም ሚዛን ተጠቅመህ ጠጉሩን ትከፍለዋለህ።
2የምርኮው ዘመን ሲያበቃ የጠጉሩን አንድ ሶስተኛ በከተማው መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ። አንድ ሶስተኛውንም ወስደህ በክተማይቱ ዙሪያ አስቀምጠህ በሰይፍ ትመታዋለህ። ከዚያም አንድ ሶስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፣ እኔም ህዝቡን አሳድድ ዘንድ ሰይፌን እመዛለሁ።
3ነገር ግን ጥቂት ጠጉሮችን ወስደህ በጋቢህ ጫፍ ላይ ትቋጥረዋለህ።
4ክዚያም በርከት ያለ ጠጉር ወስደህ ወደ እሳቱ መሀል ጥለህ በእሳቱ አቃጥለው፤ በእሳት ውስጥ ይቃጠል፤ ከዚያም ውስጥ እሳት ወደ እስራኤል ህዝብ ሁሉ ይወጣል።"
5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህች በሌሎች አገሮች ዙሪያዋን እንድትዋሰን ያደረኳት፣ በአህዛብ መካከል ያለች ኢየሩሳሌም ናት።
6ነግር ግን ከሌሎች አህዛብ ይልቅ ከኃጢእታቸው የተነሳ ትዕዛዛቴን አቃለዋል፣ በዙሪያቸው ካሉ አገሮች ይልቅ ህጌን ተላልፈዋል። ፍርዴን አቃለዋል በህጌም አልኖሩም!"
7ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በዙሪያቹ ካሉ አገሮች ይልቅ አመጸኞች ስለሆናችሁና በህጌ ስላልኖራችሁ ተግባራችሁም እንድትዕዛዛቴ ስላልሆነ ይባስ ብሎ የምታደርጉት ሁሉ በዙሪያችሁ እንዳሉት አግሮች ትዕዛዝ ስለሆነ ።"
8ስለዚህም ይላል ጌታ እግዚአብሔር "እነሆ! እኔ እራሴ በእናንተ ላይ እነሳለሁ! አህዛብ ሁሉ ያዩ ዘንድ ፍርዴን በመካከልሽ አመጣለሁ።
9ከጸያፍ ተግሮችሽ የተነሳ አድርጌ የማላውቀውን ደግሜም የማላደርገውን ነገር በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።
10ስለዚህም በመካከልሽ አባቶች ልጆቻችውን ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፣ ፍርድንም አመጣብሻለሁና የተርፉትን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ!
11ስለዚህም በራሴ እምላለሁ፦ ይህ የጌታ የእግዚአብሄር አዋጅ ነው- ቤተመቅደሴን በሚያስጠሉ ነግሮችና በሚያጸይፉ ተግባራት ሞልታችሁታልና ከቁጥር አጎድላችኋለሁ፤ ፊቴን አልመልስልሽም፣ አልራራልሽምም።
12አንድ ሶስተኛችው ህዝብ በመቅሰፍት ይሞታል በመካከልሽም በረሀብ ያልቃሉ፣ አንድ ሶስተኛው ደግሞ በከበቡሽ ጠላቶች ሰይፍ ይገደላሉ። ቀሪውን አንድ ሶስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ አሳድዳቸውም ዘንድ ሰይፌን ከሰገባው እመዛለሁ።
13ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፣ በእነርሱም ላይ የነበረኝ ንዴት ይበርዳል። በእነርሱ ላይ የነበረኝ ንዴቴ በተፈጸመ ጊዜ እኔ እግዚአብሄር በቁጣዬ እንደተናገርኳቸው ያውቃሉ።
14ዙሪያሽን በከበቡሽ አህዛብና በአላፊ አግዳሚው ሁሉ የተዋረድሽና አሳፋሪ አድርግሻለሁ።
15ስለዚህ ኢየሩሳሌም በሌሎች የምትወገዝና መቀለጃ በዙሪያዋ ላሉ አህዛብ ቁጣና ድንጋጤ ትሆናልች። ፍርዴን በንዴትና በቁጣ በጽኑ ተግሳጽም አመጣባችኋለሁ- እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
16የርሀብን አስከፊ ቀስቶች እሰድባችኋለሁ፣ ያም እናንተን የማጠፋበት መሳሪያ ይሆናል። ርሀብን አበዛለሁ የእንጀራ በትራችሁንም እሰብራለሁ።
17ልጆች አልባ እንድትሆኑ ርሀብና አደጋን እልክባችኋለሁ። መቅሰፍትና ደም በመካከላችሁ ያልፋል ሰይፍንም አመጣባችኋለሁ -- እኔ እግዚአብሄር ይህን ተናግሬአልሁ!"