መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ ሸክላ ውሰድና የኢየሩሳሌምን ካርታ ሳልበት። የጦር ከበባ አድርግባት፣
2ምሽግም ስራባት፣ ዙሪያውን በአፈር ደልድለው፣ ትልቅ ቅጥር ና የጦር ሰፈሮችን አስቀምጥ ፣ ቅጥር መደርመሻ ግንዶች ዙሪያውን አስቀምጥ።
3ክዚያም ብረት ምጣድ ለራስህ ውሰድና በአንተና በከትማይቱ መካከል በብርት አጥር ምሳሌ አቁመው። ትከበባለችና ፊትህንም ወደከትማይቱ አዙር ክበባትም! ይህም ለእስራኤል ህዝብ ምልክት ይሆናል።
4ክዚያም በግራ ጎንህ ተኛና የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአትም ተሸከም፤ በእስራኤል ህዝብ ፊት በግራ ጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር ልክ ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ።
5አንድ ቀን የሚቀጡበትን አንድ አመት እንዲወክል እኔ ራሴ መድቤልሀለሁ፡ 390 ቀናት! በዚህ መልኩ የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአት ትሸከማለህ።
6እነዚህን ቀናት ስትጨርስ በቀኝ ጎንህ ትተኛና የይሁዳን ህዝብ ኃጢአት ለአርባ ቀናት ትሸከማለህ። አንድ ቀን አንድ አመት እንዲወክል መድቤልሀለሁ።
7እጅህን ክልብስህ ውስጥ አውጥተህ ፊትህን ወደተከበበችው ኢየሩሳሌም ከተማ አድርገህ ትንቢት ትናገርባታለህ።
8እነሆ! የሜርኮው ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ጎን እንዳትዞር ቀንበርን አድርጌብሀለሁ።
9ስንዴ፣ገብስ፣ባቄላ፥ ምስር፥ ጤፍና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርገህ በጎንህ በምትተኛባቸው ቀናት ቁጥር ልክ ዳቦ ትጋግራልህ። ለ390 ቀናት ትመገበዋለህ!
10በየቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል የሚመዝን ዳቦ ትበላለህ። በየጊዜውም ትመገበዋለህ።
11አንድ ስድስተኛ ኢን ውሃም ትጠጣለህ። በየጊዜውም ትጠጣዋለህ።
12እንደ ገብስ ቂጣ አድርገህ ትበላዋለህ፣ የምትጋግረው ግን በሰው ዓይነ ምድር ነው።
13እግዚአቤሔር "በበተንኳቸው አህዛብ መካከል የእስራኤል ህዝብ የሚመገቡት ዳቦ ርኩስ ይሆናል።" ይላል።
14እኔም "ወየው ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ረክሼ አላውቅም! የሞተ ወይም በአውሬ የተገደለ በልቼ አላውቅም፣ የረከሰ ሥጋም ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም!" አልኩኝ።
15እርሱም "እነሆ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ፍግ ስጥቼሀለሁ ዳቦውን በእርሱ መጋገር ትችላለህ" አለኝ።
16ደግሞም "የስው ልጅ ሆይ! ከኢየሩሳሌም የእንጀራን በትር እሰብራለሁ፣ ህዝቡም እንጀራን በጭንቅ ውሃም በስስት ይጠጣሉ።
17የምግብና የውሃ እጥረት ስለሚኖር ሰው ወንድሙን በድንጋጤ ይመለከተዋል፣ ከኃጢአታቸው የተነሳ ይመነምናሉ።" አለኝ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።