መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 44

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር እንደገና አመጣኝ በሩም በጣም ተዘግቶ ነበር።
2እግዚአብሔርም፥ "ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ማንም አይገባበትም፥ በጥብቅ የተዘጋውም ለዚህ ነው
3የእስራኤል አለቃ በውስጡ ተቀምጦ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላል። በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።
4ቀጥሎም ከቤቱ ፊት ለፊት በሰሜኑ በር በኩል አመጣኝ። እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።
5እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ ሁሉ በዓይንህም ተመልከት በጆሮህም ስማ። የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ በል።
6ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥
7እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ እነርሱም በርኵሰታችሁ ሁሉ ላይ ይጨመሩ ዘንድ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።
8የተቀደሰውን ሥፍራዬን ኃላፊነት ለሌሎች ሰጣችሁ እንጂ ስለእኔ ያለባችሁን ግዴታ አልተወጣችሁም።
9ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ካሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
10ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።
11እነርሱ የመቅደሴ በሮች ጠባቂዎች በመቅደሴም ውስጥ አገልጋዮች ናቸው። ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ።
12ነገር ግን በጣዖቶቻቸውም ፊት መስዋዕት በማቅረባቸው ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋል። ስለዚህ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!
13ካህናትም ይሆኑኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደ ተቀደሰውም ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ነገር አይቀርቡም እፍረታቸውንና የሠሩትንም ርኵሰታቸውን ይሸከማሉ።
14ነገር ግን ለአገልግሎቱ ሁሉና በእርሱ ውስጥ ለሚደረገው ሁሉ የቤቱ ሥርዓት ጠባቂዎች አደርጋቸዋለሁ።
15ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
16ወደ መቅደሴም ይገባሉ ያገለግሉኝም ዘንድ ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴንም ይጠብቃሉ።
17ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በርና ወደ ቤቱ ውስጥ የሱፍ ልብስ ለብሰው መግባት የለባቸውም።
18በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን የሚያልብ ልብስ መልበስ የለባቸውም።
19ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ ሲወጡ ሲያገለግሉ ለብሰውት የነበረውን ልብስ ማውለቅ አለባቸው፤ በተቀደሰ ልብሳቸው ነክተው ሕዝቡንም እንዳይቀድሱ አውልቀው በተቀደሰውም ክፍል ውስጥ ያስቀምጡት።
20ራሳቸውንም አይላጩ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ።
21ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ።
22መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ብቻ ያግቡ።
23በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምራሉ፥ ንጹሁን ንጹሕ ካልሆነው መለየት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል።
24ክርክርም በሚያጋጥም ጊዜ በህጌ መሰረት ይፍረዱ፤ ፍትሀዊ መሆን አለባቸው። በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ፥ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።
25እንዳይረክሱም የአባት ወይም የእናት ወይም የወንድ ልጅ ወይም የሴት ልጅ ወይም የወንድም ወይም ከወንድ ጋር ያሌተኛች እኅት ካልሆን በስተቀር ወደ ሰው ሬሳ አይቅረቡ፤ ያለዚያ ይረክሳሉ።
26ካህን ከርከሰ ህዝቡ ሰባት ቀን ይቈጠርለት።
27በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊት፥ የኃጢአትን መሥዋዕት ለራሱ ያቅርብ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
28ይህም ርስት ይሆንላቸዋል፡ እኔ ርስታቸው እሆንላቸዋለሁ! ስለዚህ በእስራኤል ዘንድ ግዛት አትሰጡአቸው እኔ ግዛታቸው ነኝ።
29የእህሉን ቍርባንና የኃጢአትን መሥዋዕት የበደልንም መሥዋዕት ይበላሉ በእስራኤልም ለእግዚአብሔር የተለየው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
30ከበኵራቱ ሁሉ የተሻለው ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
31ካህናቱ የሞተ ወይም በአውሬ የተሰበረ ፥ ወፍ ወይም እንስሳ ቢሆን፥ አይበሉም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።