መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 43

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በር አመጣኝ።
2እነሆም፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ በኩል መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ያለ ነበር፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።
3ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ እንዳየሁትና በኮበር ወንዝ እንዳየሁት አይነት ራእይ ነበረ- እኔም በግምባሬ ተደፋሁ!
4የእግዚአብሔርም ክብር ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር ወደ መቅደሱ ገባ።
5መንፈሱም አነሣኝ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
6ሰውዬው በአጠገቤ ቆሞ ሳለ ከመቅደሱ ውስጥ የሚናገረኝን ሌላ ሰው ሰማሁ።
7እንዲህም አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ነው፤ ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በግልሙትናቸውና በጣዖት ማምለኪያ ቦታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም፡፡
8ከእንግዲህ ግንብ ብቻ በመካከል በማድርግ የጣዖቶቻቸውን መድረክ በመድረኬ አጠገብ፥ የጣዖቶቻቸውን መቃኖች በመቃኔ አጠገብ በማስቀመጥ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።
9አሁንም ግልሙትናቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከፊቴ ያርቁ፥ እኔም ለዘላለም በመካከላቸው አድራለሁ!
10አንተም የሰው ልጅ፥ ከኃጢአታቸው የተነሣ ያፍሩ ዘንድ ለእስራኤል ቤት ራስህ ልትነግራቸው ይገባል። ስለዚህ የቤቱ ዝርዝር መግለጫ ማሰብ አለባቸው።
11ከሠሩትም ሥራ ሁሉ የተነሣ ቢያፍሩ፥ የቤቱን መልክና ምሳሌውን መውጫውንም መግቢያውንም ሥርዓቱንም ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው። የቤቱን አሰራርና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው።
12የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው፡ ከተራራው ራስ ጅምሮ በዙሪያው ያለ ዳርቻ ሁሉ እጅግ የተቀደስ ይሆናል። አስተውል! የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው።
13የመሠዊያውም ልክ በረጅም ክንድ ይህ ነው፥ ይህም ማለት አንድ ክንድ ከጋት ነው። በመሰዊያው ዙሪያ ያለው አሸንዳ ቁመቱ አንድ ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። የዙሪያው ጠርዝ አንድ ስንዝር ነው። ይህም የመሰዊያው መሠረት ነው።
14በመሬቱም ላይ ካለው አሸንዳ ጀምሮ እስከ ታችኛው የመስዊያው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። ከመሰዊያው ትንሹ ጠርዝ እስከ ትልቁ ጠርዝ ድረስ አራት ክንድ፥ የሰፊው ጠርዝ ስፋትም አንድ ክንድ ነው።
15ለሚቃጠል መስዋዕት የሚያገለግለው በመሰዊያው ላይ ያለው ምድጃ አራት ክንድ ነው፥ በምድጃውም ላይ ጫፋቸው ወደላይ የቆመ ቀንዶች አሉበት።
16ምድጃውም አራት ማዕዘን ሆኖ ርዝመት አሥራ ሁለት ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነው።
17ጠርዙም በአራቱም ማዕዘን አሥራ አራት ክንድ ወርዱም አሥራ አራት ክንድ ነው፥ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ነው። አሽንዳውም ወደምስራቅ ከሚያመለክቱት ደረጃዎቹ ጋር ዙሪያውን አንድ ክንድ ነው።
18ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ ደሙንም ይረጩበት ዘንድ መሰዊያውን በሚሠሩበት ቀን የመሠዊያው ሕግ ይህ ነው።
19ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
20ከደሙም ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹም በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ በዙሪያውም ባለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታስተሰርይለትማለህ።
21ለኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ በመቅደሱም ውጭ በተዘጋጀለት ስፍራ ታቃጥለዋለህ።
22በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ ካህናቱም በወይፈኑ ደም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።
23ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ነውር የሌለበትን ወይፈንና ከመንጋው የወጣውን ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ።
24በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፥ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።
25ለሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ካህናቱም ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ።
26ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹትማል፥ እንዲሁም ይቀድሱታል።
27እነዚህ ቀኖችንም መፈጸም አለባቸው፥ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።