1በመቀጠልም ሰውዬው በውጭ በሰሜን አቅጣጫ ወደሚገኘው አደባባይ አወጣኝ፥ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል ባለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳሉ ክፍሎች አመጣኝ ።
2ክፍሎቹም በፊት ለፊት ገጽታቸው መቶ ክንድ ስፋታቸውም አምሳ ክንድ ነበረ።
3ከእነዚህ ክፍሎች አንዳንዶቹ ፊታቸው ወደ ግቢው ወስጥ ነበር ከቤተመቅደሱም ሃያ ክንድ ይርቁ ነበር። ባለ ሶስት ደርብ ክፍሎችም ነበሩ። ከላይ ያለው ክፍል ወደታችኛው ክፍሎች ይመለከትና ለእነርሱ ክፍት ነበር መላለፊያ መንገድም ነበረው። የተወሰኑት ክፍሎች ወደ ወደውጪኛው አደባባይ ይመለከቱ ነበረ።
4ከክፍሎቹም ፊት በስተ ውስጥ ወርዱ አሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ ነበረ። የክፍሎቹም መዝጊያዎች ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር።
5ነገር ግን መተላለፊያው ከህንጻው መካከለኛና ከታችኛው ክፍል በላይ ቦታቸውን የያዘ በመሆኑ የላይኞቹ ክፍሎች ትንንሽ ነበሩ።
6በሦስት ደርብ በመስራታቸውና በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ ያሉ፥ አዕማድ ስላልነበሯቸው ላይኞቹ ደርቦች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ
7የውጪው ግንብ ከክፍሎቹና ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ከሚገኘው ክውጭው አደባባይ ትይዩ ይገኛል ፥ ርዝመቱም አምሳ ክንድ ነበረ።
8በውጪኛው አደባባይ ርዝመቱ ሃምሳ ክንድ ሲሆን በመቅደሱ ፊት የነበሩት ክፍሎች ደግሞ ርዝመታቸው መቶ ክንድ ነበረ።
9ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ከውጭው አደባባይ የሚጀምር መግቢያ ነበረ።
10በምስራቅ በኩል የውጭውን አደባባይ ተከትሎ ከቤተመቅደሱ ውስጠኛ አደባባይ ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ።
11በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በርዝመቱና በወርዱ በሰሜን በኩል ከነበሩት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን መግቢያዎቻቸውም በቁጥር እኩል ነበሩ።
12በደቡብም በኩል ልክ በሰሜን በኩል እንዳለው ወደ ክፍሎቹ የሚያስገቡ መግቢያዎች አሉ። በውስጥ በኩል ያለው መተላለፊያ ከበላዩ መግቢያ ያለው ሲሆን መተላለፊያው ወደተለያዩ ክፍሎች ያመሩ ነበር። በምስራቅ በኩል ወደ መተላለፊያው አንደኛው ጫፍ የሚያመራ መግቢያ ነበር።
13ከዚያም እንዲህም አለኝ፥ "በውጭኛው አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኙት የሰሜንና የደቡብ ክፍሎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው የተቀደሱ ክፍሎች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ስለሆን በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቍርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያስቀምጣሉ።
14ካህናቱም አንድ ጊዜ ወደዚያ ከገቡ ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ቅዱስ በመሆናቸው ሳያወልቁ ከተቀደሰው ሥፍራ ወደውጭኛው አደባባይ መውጣት የለባቸውም። ስለዚህም ወደ ሕዝቡ ከመጠጋታቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።
15ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በር አወጣኝና ዙሪያውን ሁሉ ለካ።
16የምሥራቁን ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
17የሰሜኑንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
18የደቡቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
19ዞረም፥ የምዕራቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
20በአራቱ ወገን ለካው። የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።