መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 41

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ሰውዬው ወደ መቅደሱም ቅዱስ ስፍራ አገባኝ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ።
2የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ።ቀጥሎም ሰውዬው ቅዱስ ስፍራውን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሀያ ክንድአድርጎ ለካ።
3ከዚያም ሰውዬው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ገባ፥ የመግቢያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ። የመግቢያውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ በዚያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።
4የክፍሉንም ርዝመት ወደ መቅደሱ ፊት ለፊት ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፥ "ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው" አለኝ።
5የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ አድርጎ። በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ ነበረ።
6ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ድጋፍ የሆኑ መደርደሪያዎች ነበሩ፥ ምክንያቱም በመቅደሱ ግንብ ውስጥ ድጋፎች አልነበሩም።
7ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ።
8በመቅደሱም ዙሪያ የጓዳዎቹም መሠረት የሆነ ከፍ ያለ ወለል እንዳለ አየሁ ቁመቱም ሙሉ ዘንግ የሚያህል ስድስት ክንድ ነበረ።
9የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ። በመቅደሱም ጓዳዎች ውጭ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ።
10በዚህም ባዶ ስፍራ በአንድ ወገን የካህናት በረንዳዎች ነበሩ፤ የባዶውም ስፍራ ወርድ በዙሪያ አምስት ክንድ ነበረ። ይህም ባዶ ሥፍራ በመቅደሱ ዙሪያ ወርዱ ሀያ ክንድ ነበረ።
11በዚህም በባዶው ስፍራ አንዱ በሰሜን በኩል አንዱም በደቡብ በኩል የጓዳዎች መግቢያ ነበረ። የባዶውም ስፍራ ዙሪያ ወርድ አምስት ክንድ ነበረ።
12በምዕራብም በኩል ባለው ግቢ አንጻር ያለው ህንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።
13የመቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
14ደግሞም ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የሚገኘው ግቢ የፊት ለፊት ወርዱ አንድ መቶ ክንድ ነበር።
15ቀጥሎም ሰውዬው ከቤተ መቅደሱ በስተዋላ ያለውን ህንጻ የምዕራብ ክፍል በዚህና በዚያ ከነበሩት ፎቆች ጋር እንዲሁም ቅዱስ ስፍራውና መድረኩን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
16ውስጠኛዎቹ ግድግዳዎች፥ ጠባቦቹን ጨምሮ መስኮቶቹ እንዲሁም በሶስት ደረጃዎች ያሉ ፎቆች በእንጨት ተለብጠው ነበር።
17ከደጁም በላይ እስከ ውስጠኛው ክፍል ድረስ፥ በውጭም ግንቡ ሁሉ ውስጡም ውጭውም ተለብጦ ነበር።
18በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውቦ ነበር የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።
19የሰው ፊት የሚመስለው በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት የሚመስለው ደግሞ በሌላ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር። ይህም በዙሪያ ያሉትን ቤቶች አስውቦ ነበር።
20ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ አናት ድረስ እና በመቅደሱ ላይ በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውበው ነበር።
21የመቅደሱ መቃኖችም አራት ማዕዘን ነበሩ፥ ሁሉም ለእርስ በእርስ ትይዩ ነበሩ።
22ከቅዱሱ ሥፍራ ፊት ለፊት የሚገኘው ከእንጨት የተሰራው መስዋዕት ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱም ሁለት ክንድ ነበር። ማዕዘኖቹም እግሩም አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር። ሰውዬውም ፥ "ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ናት" አለኝ።
23ለተቀደሰው ስፍራና ለቅድስተ ቅዱሳኑ ሁለት መዝጊያዎች ነበሩአቸው።
24ለእያንዳንዱ መዝጊያም ሁለት ተዘዋዋሪ ሳንቃዎች ነበሩት ለአንዱ መዝጊያ ሁለት ለሌላውም መዝጊያ ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት።
25ግንቦቹን እንዳስዋቡት ዓይነት በእነዚህ በቅዱስ ስፍራው መዝጊያዎች ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፣ በስተ ውጭም ባለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእንጨት ጣራ ነበረ።
26በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ ጠባብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት። እነዚህም የመቅደሱም ጓዳዎች ነበሩ ፥ እነርሱም ተንጠልጣይ ጣሪያዎችም ነበሯቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።