1የሰው ልጅ ሆይ ያገኘኽውን ብላ ይህን የመጽሀፍ ጥቅል ብላ ሄደህም ለእስራኤል ህዝብ ተናገር።
2አፌንም ከፈትኩ የመጽሀፉን ጥቅል አጎረሰኝና
3"የሰው ልጅ ሆይ በሰጠሁህ በዚህ የመጽሀፍ ጥቅል ሆድህን ሙላ" አለኝ። እኔም በላሁት እንደማርም ጣፈጠኝ።
4ከዚያም "የሰው ልጅ ሆይ ወደ እስራኤል ህዝብ ሄደህ ቃሌን ንገራቸው" አለኝ።
5ምክንያቱም የተላከው ቋንቋቸው ወደማይታወቅ ወይም አስቸጋሪ ወደሆን ህዝብ አይደለም፦
6እንግዳ ቋንቋ ወደሚናገር ታላቅ ህዝብ ወይም የቋንቋቸውን ቃላት መረዳት ወደሚያስቸግር ህዝብ አላኩህም። ወደዚህ ዓይነት ህዝብ ብልክህ ኖሮ ይሰሙህ ነበር። ነገር ግን የእስራኤል ህዝብ እኔን መስማት ስለማይፈልጉ አይሰሙህም።
7የእስራኤል ህዝብ ሁሉ ግንባረ ጠንካራና አንገተ ደንዳና ናቸው።
8እነሆ! ፊትህን እንድፊታቸው ግንባርህንም እንደግንባራቸው ጠንካራ አደርገዋለሁ።
9ግንባርህን ከባልጩት ድንጋይ ይልቅ እንደሚጠነክር እንደ አልማዝ አድርጌዋለ! ስለዚህ የእሴራኤል ህዝብ አመጸኞች ስለሆኑ አትፍራቸው ፊታቸውንም አይተህ አትደንግጥ።
10ቀጥሎሜ እንዲህ አለኝ "የሰው ልጅ ሆይ የነገርኩህን ቃል ስማ በልብህም ተቀበለው።
11ከዚያም በምርኮ ወዳሉት ህዝብህ ሂድና ቢሰሙህም ባይሰሙህም 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' በላቸው።"
12መንፈስም ከምድር ከፍ አደረግኝ ከኋላዬም የእግዚአብሔር ክብር በማደሪያው ይባረክ የሚል እንደ ምድር መናወጥ ዓይነት ድምጽ ሰማሁ።
13ወዲያውም የህያው ፍጥርታቱ ክንፎች ሲነካካ የሚፈጠረውን ድምጽ፣ አብረዋቸው ያሉትን መንኮራኩሮች ድምጽ፥ እና የምድር መናወጥ ድምጽ ሰማሁ።
14መንፈስም አንስቶ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም እጅ በእኔ ላይ ከብዶ ስለነበር የምሄደው በምሬትና በጋለ መንፈስ ነበር።
15ከዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ወደሚኖሩት በቴላቢብ ወደሚገኙት ምርኮኞች ሄጄ በድንጋጤና በመደነቅ ተሞልቼ በመካከላቸው ሰባት ቀን ተቀመጥኩ።
16ከስባት ቀንም በኋላ እንዲህ ሆነ፥
17"የሰው ልጅ ሆይ አንተን ለእስራኤል ህዝብ እንደጠባቂ አድርጌሀለሁ፥ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማና የእኔን ማስጠንቀቂያ ንገራቸው!
18ኃጢአተኛውን 'በእርግጥ ትሞታለህ' ብለህ ንገረው ብዬህ አንተ ግን ባትነግረው ከክፉ መንገዱም እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
19ነገር ግን ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከክፋቱና ከመጥፎ ተግባሩ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተም ነፍስህን ታድናለህ።" ብሎ እግዚአብሔር ሲናገረኝ ሰማሁ።
20ደግሞም አንድ ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረግን ቢተው እኔም በፊቱ መሰናክል ሳስቀምጥ እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል። አንተ ስላላስጠነቀከው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፣ ቀድሞ የሰራውንም የጽድቅ ስራ አላስብለትም፣ ነገር ግን አንተን የሞቱ ተጠያቂ አደርግሀለሁ።
21ነገር ግን አንድ ጻድቅ ሰው ኃጢአት መስራቱን እንዲያቆም ብታስጠነቅቀው ከማስጠንቀቂያው የተነሳ በእርግጥኝነት በህይወት ይኖራል፣ አንተም የራስህን ህይወት ታድናለህ።"
22ደግሞም የእግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣ፣ እግዚአብሔርም ፣ "ተነሳ! ወደ ሜዳማው ቦታ ሂድ፣ በዚያ የምነግርህ ነገር አለ" አለኝ።
23እኔም ተነስቼ ወደ ሜዳማው ቦታ ሄድኩ፥ በዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ያየሁት ዓይነት የእግዚአብሔር ክብር ነበረ፣ ስለዚህም በግንባሬ ተደፋሁ።
24የእግዚአብሔርም መንፈስ መጥቶ በእግሮቼ አቆመኝና እንዲህ ሲል ተናገረኝ "ወደ ቤትህ ሂድና በር ዘግተህ ተቀመጥ፣
25ምክንያቱም አሁን የሰው ልጅ ሆይ በመካከላቸው እንዳትንቀሳቀስ በገመድ ያስሩሀል።
26አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ እንዳትገስፃቸው እኔ ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቀዋለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ።
27ነገር ግን እኔ ስናገርህ አፍህን እከፍታለሁ አንተም 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' ትላቸዋለህ፤ አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ የሚሰማ ይሰማሀል የማይሰማ አይሰማህም!"