መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 38

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥
3እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።
4እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ!
5ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱት ፋርስን ኢትዮጵያና ፉጥ ከእነርሱ ጋር ናቸው!
6ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎች ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ናቸው።
7ተዘጋጅ! አዎ፥ ራስህንና ሠራዊትህን አዘጋጅ አለቃም ሁናቸው።
8ከብዙ ቀናትም በኋላ ትጠራልህ ክተወሰኑ ዓመታት በኋላ ክሠይፍ እያገገመች ወዳለችው፥ ከብዙ ሕዝቦችም መካከል ተሰብስበው ያለማቋረጥ ባድማ በነበሩት በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግም ወደ ተሰበሰቡ ትሄዳለህ። የምድሪቱ ሕዝብ ግን ከሕዝቦች መካከል ወጥተው ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።
9አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።
10ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን በልብህ ታቅዳለህ፥
11ክፉ አሳብንም ታስባለህ።' እንዲህም ትላለህ፥ 'ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ
12ባድማም በነበሩና በቅርቡ ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከብትና ዕቃንም ይዘው ከአሕዛብም በተሰበሰቡ ሰዎች በምድርም መካከል በሚኖሩ ሕዝብ ላይ እጄን እዘረጋናምርኮን እማርካለሁ ብዝበዛንም እበዘብዛለሁ ።
13ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች ከወጣት ጦረኞቻችው ሁሉ ጋር እንዲህ ይሉሀል፥ 'የመጣኸው ምርኮን ለመማረክ ነው? ጦርህን የሰበሰብከው ብዝበዛን ለመበዝበዝ ብርንና ወርቅንስ ለመውሰድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ለመውሰድ እጅግም ብዙ ምርኮ ለመማረክ ነው?'።
14ስለዚህም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ ስለእነርሱ አታውቀውምን?
15አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።
16ደመና ምድርን እንድሚሸፍን ህዝቤን ታጠቃለህ። ጎግ ሆይ እንዲህ ይሆናል በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
17ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ አይደለህምን?
18በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
19በቁጣዬ ትኩሳትና በመዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥ በእርግጥ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ የምድር መናወጥ ይሆናል።
20የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ። ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
21በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
22በቸነፈር፥ በደም ፥በዶፍ ዝናብና የድንጋይ እሳት እፈርድባቸዋለሁ። ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።
23ታላቅነቴንና ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።