1አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው ፥ 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!'
2ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ "እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል" ብሎአል።
3ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባድማ በመሆናችሁና ከሁሉም አቅጣጫ ከመጣባችሁ ጥቃት የተነሳ ለሌሎች አሕዛብ ርስት ሆናችኋል፤ የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫም ሆናችኋል።
4ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆች ለምድረ በዳዎች ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል
5ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በወሰዱ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ
6ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶችም ለፈሳሾችና ለሸለቆችም እንዲህ በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ
7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ስድባቸውን በእርግጥ ይሸከማሉ ብዬ ምያለሁ።
8እናንተ የእስራኤል ተራሮች ግን ወደ እናንተ ተመልሰው የሚመጡበት ቀን ቀርቧልና፥ ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤልም ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ።
9እነሆ፥ እኔ ለእናንተ ነኝና ወደ እናንተም እመለከታለሁ፥ እናንተም ትታረሳላችሁ ይዘራባችሁማል።
10ስለዚህም እናንተ ተራሮች ሆይ በእስራኤል ቤት ሁሉ ሰዎችን አበዛባችኋለሁ። ሁሉም! ከተሞች የሰዎች መኖሪያ ይሆናሉ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።
11እናንተ ተራሮች ሆይ ሰውንና እንስሳውንም አበዛባችኋለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈሩማል። ቀድሞ እንደነበራችሁት የሰዎች መኖሪያ አደርጋችኋለሁ፥ ከቀድሞ ይልቅ አበለጥጋችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
12በእናንተ ላይ እንዲረማመዱ የሕዝቤን የእስራኤልን ሰዎችን አመጣቸዋለሁ። እነርሱም ይወርሱዋቸዋል ርስትም ትሆኑላቸዋላችሁ፥ ከእንግዲህም የልጆቻቸው ሞት ምክንያት አትሆኑም።
13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ "እናንተ ሰው በሊታ ናችሁ የሕዝባችሁም ልጆች አልቀዋል" ብለዋችኋልና
14ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሰው በሊታ አትሆኑም፥ ዳግመኛም ሕዝብችሁን በሚሞቱ ሰዎች ምንንያት እንዲያለቅሱ አታደርጉም ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
15ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
16የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
17"የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ።
18በምድሪቱም ላይ ስላፈሰሱት ደም በጣዖቶቻቸውም ስላረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው።
19ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው።
20ወደ ሌሎች ሕዝቦች ሄዱ። በሄዱም ጊዜ ሰዎች ስለነርሱ 'አሁን እነዚህ ከአገራቸው የተፈናቅሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው?' በማለታቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ።
21እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው።
22ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን የማደርገው በሄዳችሁበት በአሕዛብ መካከል ሁሉ ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ አይደለም።
23በአሕዛብም ዘንድ የረከሰውን፥ በመካከላቸው ያረከሳችሁትን ስሜን እቀድሰዋለሁ። በዓይናቸውም ዘንድ በተቀደስሁባችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
24ከአሕዛብም መካከል እወስዳችኋለሁ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ።
25ከእርኩሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹም ጥሩ ውኃን እረጭባችኋለሁ። ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።
26አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
27መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም መሄድ አስችላችኋለሁ ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
28ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ ሕዝቤ ትሆናላችሁ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።
29ከርኵሰታችሁም ሁሉ አድናችኋለሁ እህልንም እጠራዋለሁ አበዛውማለሁ ከእንግዲህም ራብን አላመጣባችሁም።
30ደግሞም የራብን ስድብ በሕዝቦች መካከል እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን ቡቃያ አበዛለሁ።
31ከዚያም ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
32ይህን ያደረኩት ስለ እናንተ ብዬ እንዳይደለ እወቁ-ይላል ጌታ እግዚአብሔር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።
33ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ክእርኩሰታችሁ ሁሉ ባነጻኋችሁበት ቀን በከተሞቻችሁ እንድትኖሩ የፈረሱትንም ሥፍራዎች እንደገና እንድትጠግኑ አደርጋችኋለሁ።
34ባድማ የነበረች ምድር በመንገደኛ ሁሉ ዓይን ባድማ ባል ድረስ ትታረሳለች።
35ሰዎችም፥ "ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል" ይላሉ።
36በዙሪያችሁም ያሉ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ ውድማ የሆነውንም እንደገና እንደተከልሁ ያውቃሉ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ።
37ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ እንደመንጋ እንዳበዛቸው የእስራኤል ቤት ይጠይቁኛል።
38ለእግዚአብሔሬእንደ ተለዩ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች፥ እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።