1እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በለው፥ 'በእህዛብ መካከል እንደ አንበሳ ደቦል በባህር እንዳለ አስፈሪ ፍጥረት ነበርክ፤ ውሃውን አናወጥከው፥ ውሆችን በእግርህ በጥብጠህ አጨቀየሀቸው።
3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፥ እነርሱም በመረቤ ይይዙሀል!
4በምድርም ላይ እተውሃለሁ፥ በምድረ በዳም ፊት እጥልሃለሁ፥ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፥ የተራቡ ምድርን አራዊት በአንተ አጠግባቸዋለሁ።
5ሥጋህን በተራሮች ላይ አደርጋለሁ ሸለቆቹንም በትል በተሞላ ሬሳህ እሞላለሁ!
6ደምህንም በተራሮች ላይ አፈሳለሁ መስኖችም በደምህ ይሞላሉ።
7መብራትህን ባጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶችንም አጨልማለሁ። ፀሐይንም በደመና እሸፍናለሁ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም!
8የሰማይን ብርሃኖች ሁሉ በላይህ አጨልማለሁ፥ በምድርህም ላይ ጨለማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
9በአዛብ መካከል ጥፋትህን በማመጣ ጊዜ የማታውቃቸውን የብዙ ሕዝብን ልብ አስደነግጣለሁ።
10ብዙም አሕዛብን ስለዘንተ አስደንቃለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ስለ አንተ እጅግ አድርገው ይፈራሉ። በውድቀትህም ቀን እያንዳንዱ በአንተ ምክንያት ይንቀጠቀጣል።
11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።
12አገልጋዮችህ የአህዛብ ድንጋጤ በሆኑ ጦርኞች ሥይፍ እንዲወድቁ አደርጋልሁ! የግበጽንም ትዕቢት ያውርዳሉ ህዝቧንም ሁሉ ያጠፋሉ!
13እንስሶችን ከብዙ ውኃ አጠገብ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የሰው እግርም ሆነ የእንስሳት ኮቴ ውሃውን አያደፈርስም!
14በዚያን ጊዜ ውኃቸውን አረጋጋለሁ፥ እንደ ዘይትም እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
15ሙሉ የነበረውን የግብጽን ምድር ባድማና ውድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ!
16የአሕዛብ ቈነጃጅት ያለቅሱበታል ያለቅሱባታልና ሙሾ ይሆናል፥ ነው ስለ ግብጽና ስለአገልጋዮቿ ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
17እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
18የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ አገልጋዮች አልቅስ፥ እርስዋንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
19እንዲህ ብለህ ጥይቃቸው፥ 'ከማንም ይልቅ በውበት ትበልጣላችሁን? ውረዱና ካልተገረዙትም ጋር ተኙ!
20በሰይፍ በተገደሉት መካከል ይወድቃሉ፤ ጥላቶቿ እርሷንና አገልጋዮቿን ይይዛሉ!
21በሲኦል የኃያላን አለቆች ስለ ግብጽ ፥ "ወደዚህ ወደ ሲዖል መጥተዋል! በሰይፍ ከተገድሉ ካልተገርዙት ጋር ይተኛሉ!' ብለው ይናገራሉ።
22አሦርና ጉባኤዋ ሁሉ በዚያ አሉ መቃብሮችም ከበዋታል፤ ሁሉም በሰይፍ የተገደሉ ናቸው።
23መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል የሆኑትም ከእርሷ ጉባኤ ሁሉ ጋር በዚያ አሉ! መቃብሯ በተገደሉ፥ በሰይፍ በወደቁ እንዲሁም በሕያዋን ምድር ፍርሀትን ባመጡ ተከቧል።
24ኤላምም ከአገልጋዮቿ ጋር በዚያ አለች፤ መቃብሮቿም ከበዋታል። ሁሉም የተገደሉ ናቸው። እነርሱም በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ ፥ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር የወረዱ፥ በህያዋን ምድር ሽብርን ያመጡና ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን የተሸከሙ ናቸው።
25በተገደሉት መካከል ለኤላምና ለአገልጋዮቻ መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው! ሁሉም ያልተገረዙና በህያዋን ምድር ሽብርን በማምጣታቸው በሰይፍ የተገደሉ ናቸው! ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል። ኤላምም በተገደሉትም መካከል ነች።
26ሞሳሕና ቶቤል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሕያዋን ምድር ሽብር ያመጡ ስለነበር በሰይፍ የተገደሉ ናቸው!
27በሕያዋንም ምድር ኃያላኑን ያስፈሩ ነበርና መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ካደረጉ፥ ካልተገረዙ ኃያላን ጋር አልተኙምን? በህያዋን ምድር አስፈሪ ተዋጊዎች በመሆናቸው ጋሻቸውም በአጥንታቸው ላይ ነው ።
28አንቺም ግብጽ ባልተገረዙት መካከል ትሰበሪያለሽ! በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትተኚያለሽ።
29ኤዶምያስ ከነገሥታቶችዋና ከአለቆችዋ ሁሉጋር በዚያ አሉ። ኃያላን ነበሩ፥ ነገር ግን አሁን በሰይፍ ከተገደሉትና ካልተገረዙት ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ይተኛሉ ።
30የሰሜን አለቆች ሁሉ ከሙታን ጋር የወረዱ ከሲዶናውያንም በዚያ አሉ! ኃያላን ነበሩ፥ አሁን ግን በዚያ በእፍረት ፥ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል። እፍረታቸውን ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ይሸከማሉ።
31ፈርዖንም ይመለከታል በሠይፍ ስለተገደሉት አገልጋዮቹ ይጽናናል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
32መፈራቱን በሕያዋን ምድር አድርጌአለሁ፥ ነገር ግን በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ይተኛል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"