1"የሰው ልጅ ሆይ ተነስና ቁም ክዚያም አነጋግርሃልሁ" አለኝ።
2እየተናገረኝ ሳለ መንፈስ አንስቶ በእግሮቼ አቆመኝ የናገረኝንም ሰማሁ።
3"የሰው ልጅ ሆይ አመፀኛ ወደሆኑትና በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ እስራኤል ህዝብ እልክሃለሁ፦ እነርሱና የቀደሙ አባቶቻችው እስከዚች ቀን ድረስ በድለውኛል!
4ልጆቻቸው የተጨማደደ ፊትና ደንዳና ልብ አላቸው። አንተም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ትላቸዋለህ።
5አመጸኛ ቤት ስለሆኑ ወይ ይሰሙሃል አሊያም አይሰሙህም። ነገር ግን ቢያንስ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።
6አንተም የሰው ልጅ ሆይ እነርሱንም ሆነ ቃላቸውን አትፍራ። በእሾሆች፣በኩርንችት እና በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። አመጸኛ ቤቶች ስለሆኑ ቃላቸውን አትፍራ ፊታቸውን አይተህ አትደንግጥ።
7እጅግ አመጸኞች ስለሆኑ ቢሰሙህም ባይሰሙህም ቃልን ትነግራቸዋለህ።
8ነገር ግን አንተ የሰው ልጅ የምነግርህን ስማ። አንተም እንደአመጸኞቹ ሰዎች አመጸኛ አትሁን። አፍህን ክፈትና የምሰጥህን ብላ።
9ጽሁፍ የተጻፈበት ጥቅል የያዝ እጅ ወደኔ ሲዘረጋ አየሁ።
10በፊቴም ዘረጋው ክፊትና ከኋላው ተጽፎበት ነበር፤ በሀዘን፣ በልቅሶና በዋይታ የተሞላ ነበር።