1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
2"አንተ የሰው ልጅ ሆይ እንግዲህ ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ ጀምር ጢሮስንም እንዲ በላት
3'አንቺ በባሕር መግቢያ የምትኖሪ በብዙም ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ህዝቦች ጋር ንግድን የምታደርጊ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ። 'በውበት ፍጹም ነኝ ብለሻል!
4ዳርቻሽ በባሕር ውስጥ ነው የሰሩሽ ፍጹም ውብ አድርገውታል።
5ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሳኔር ጥድ ሠርተዋል፥ ደቀልንም ሊሰሩልሽ ከሊባኖስ ዝግባ ወስደዋል።
6ከባሳን ዛፍ መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፥ በዝሆን ጥርስ ከታሸበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ የመርከብ ወለሎችሽን ሠርተዋል።
7የመርከብሽ ሸራ ልክ እንደ ሰንደቅ ዓላማሽ የግብጽ ባለብዙ ቀለማት በፍታ ጨርቆች ነበሩ።
8የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፤ የጢሮስ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ።
9ልምድ ያላቸው ጥበበኞች መጋጠሚያዎችሽን ሞልተዋል። የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው የንግድ እቃዎችሽን ለንግድ ያጓጉዙልሻል።
10ፋርስና ሉድ ፉጥም በሠራዊትሽ ውስጥ ነበሩ፥ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፥ እነርሱም ውበትሽን አሳዩ።
11በሠራዊትሽ ውስጥ የነበሩት የአራድ እና የኤሌክ ሰዎች በቅጥሮችሽ በዙሪያ ነበሩ፥ ገማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ! ጋሻቸውንም ዙሪያውን በቅጥርሽ ላይ አንጠለጠሉ! ውበትሽንም ፍጹም አደረጉት!
12በብዙ ዓይነት ማለትም በብር፥ በብረት ፥ በቈርቈሮና በእርሳስ ካለሽ ብልጥግና ብዛት የተነሣ ተርሴስ የንግድ ደንብኛሽ ነበረች። ሸቀጥሽን ይገዙና ይሸጡ ነበር።
13ያዋንና ቶቤል ሞሳሕም ባሮችንና ከናስ የተሰሩ እቃዎችን ይነግዱ ነበር። ንግድሽን የሚመሩት እነርሱ ነበሩ።
14ከቤተ ቴርጋማም መጋዣዎችን፥ የጦር ፈረሶችንና በበቅሎዎችን ወደ ንግድሽ አመጡ።
15የድዳን ሰዎች በብዙ ዳርቻዎችሽ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። ንግድ በእጅሽ ነበረ፤ በሸቀጥሽ ምላሽ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ይልኩልሽ ነበር።
16ሶርያ የብዙ ምርቶችሽ ተጠቃሚ ነበረች። በልዋጩም የከበረ ድንጋይ፥ የወይን ጠጅ፥ ባለ ብዙ ቀለም ልብሶች፥ ያማሩ ጨርቆች፥ በዛጎል እና ቀይ ዕንቍም ያቀርቡ ነበር።
17ይሁዳና የእስራኤል ምድር የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጐቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ያቀርቡ ነበር።
18ደማስቆ የምርትሽ ሁሉ፥ ተዝቆ የማያልቅ ሀብትሽ እንዲሁም የኬልቦን የወይን ጠጅና የዘሀርን የበግ ጠጕር ይነግዱ ነበር።
19ዌንዳንና ያዋን ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር። ቀልጦ የተሠራ ብረት፥ ብርጕድና ቀረፋም ያቀርቡ ነበረ። ይህም ላንቺ ንግድ ሆነልሽ
20ድዳን የግላስ ንግድ ከአንቺ ጋር ነበራት።
21ዓረብና ሌሎች የቄዳር አለቆች ሁሉ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ፤ ጠቦቶች፥ አውራ በጎችና ፍየሎችን ለንግድ ያቀርቡልሽ ነበር።
22የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ምርጥ የሆነ የቅመም ሽቱ ሁሉና ብዙ ዓይነት የከበሩ ድንጋዮች ሊሸጡልሽ ይመጡ ነበር። ወርቅም ይነግዱ ነበር።
23ካራንና ካኔ ዔድንም ከሳባ፥ ከአሦርና ከኪልማድ በመሆን የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ።
24እነዚህ ባማረ ልብስ በሰማያዊ ካባ በወርቀ ዘቦም፥ በዝግባ በተሠራች በገመድም በታሰረች በግምጃም በተሞላች ሳጥን ይነግዱ የነበሩ ናቸው።
25የተርሴስ መርከቦች የሸቀጥሽ ማጓጓዣዎች ነበሩ። አንቺም በባህር መካከል ተሞልተሽ በጭነትም ከብደሽ ነበር።
26ቀዛፊዎችሽ ወደ ስፊ ባህሮች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስም በባህሮቹ መካከል ሰበረሽ።
27በውድቀትሽ ቀን ብልጥግናሽ፥ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃዎችሽ፤ የመርከብ ነጂዎችሽ፥ መርከበኞችሽም መርከብ ሠሪዎችሽ፤ ነጋዴዎችሽ ሁሉ በአንቺም ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በውስጥሽ ካሉት ሠራተኞች ጋር ወደ ባሕር ጥልቅ ይወድቃሉ።
28ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ በባህር አጠገብ ያሉ ከተሞች ይንቀጠቀጣሉ።
29ቀዛፊዎችም ሁሉ መርከበኞችም መርከብ መሪዎችም ሁሉ ከመርከቦቻቸው ወርደው በመሬት ላይ ይቆማሉ።
30ከዚያም ድምፃቸውን እንድትሰሚ ያደርጉሻል ምርር ብለውም ይጮኻሉ፥ ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ይነሰንሳሉ፥ በአመድም ውስጥ ይንከባለላሉ
31ስለ አንቺም የራሳቸውን ጠጕር ይላጫሉ ማቅም ይታጠቃሉ በምሬትም ስለአንቺ ያነባሉ ይጮኸሉ።
32በትካዜያቸውም ልቅሶ ያነሡልሻል፥ ስለ አንቺም ሙሾ ያሞሻሉ እንዲህም ይላሉ። በባሕር መካከል ጠፍቶ እንደ ቀረ እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?
33ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን ያጠግብ ነበር በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል።
34ነገር ግን በጥልቅ ውኃ ውስጥ በባህር በተሸፈንሽ ጊዜ ንግድሽና ሠራተኞችሽ ሁሉ ሰጠሙ!
35በባህር ዳርቻ የሚኖሩ ሁሉ ተደንቀውብሻል፥ ነገሥታቶቻቸውም በፍርሀት ተንቀጥቅጠዋል። ፊታቸውም ደንግጧል።
36የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፤ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ ከእንግዲህ በኋላም አትኖሪም።