1እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፡
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ። 'እሰይ፥ የአሕዛብ በር የነበረች ተሰብራለች ወደ እኔም ተመልሳለች እርስዋ ፈርሳለችና እኔ እሞላለሁ!' ብላለች።
3ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ "ጢሮስ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ ህዝቦችን በአንቺ ላይ አስነሳልሁ።
4የጢሮስንም ቅጥሮች ያጠፋሉ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ ትቢያዋንም ከእርስዋ እጠርጋለሁ፥ የተራቈተ ድንጋይም አደርጋታለሁ።
5በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር ለአሕዛብም ብዝበዛ ትሆናለች።
6በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
7ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
8በሜዳ ያሉትን ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ ምሽግም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል።
9ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ መሳሪያውም ግንቦችሽንም ያፈርሳል!
10ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል! ሰዎችም በፈርሰ ቅጥር በኩል ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኰራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ይናወጣል።
11በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፤ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል።
12በዚህ መንገድ ብልጥግናሽንም ሸቀጥሽንም ይዘርፋሉ! ቅጥርሽንም ያፈርሳሉ፥ ተድላ የምታደርጊባቸውን ቤቶችሽን ያጠፋሉ ድንጋይሽንና እንጨትሽን መሬትሽንም በባሕር ውስጥ ይጥላሉ።
13የዝማሬ ጩኸትሽን ዝም አሰኛለሁ የክራሮች ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይሰማም!
14የተራቈተ ድንጋይ አደርግሻለሁ የመረብም ማስጫ ትሆኛለሽ። ከእንግዲህ እንደገና አትገነቢም እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር!
15ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላታል፥ 'በውስጥሽ እልቂት በሆነ ጊዜ በውድቀትሽ ጩኸትና በቆሰሉ ሰዎች የሥቃይ ድምጽ የተወጉት ባንቋረሩ ጊዜ፥ ፥ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን?
16የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ ስለአንቺም ይፈራሉ።
17በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፥ እንዲህም ይሉሻል። የመርከበኞች መኖሪያ የነበርሽ እንዴት ወደምሽ! ዝናሽ የወጣ ጠንካራ ከተማ አሁን ግን ከባህር ጠፋሽ! በአንድ ወቅት በእርሷ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አስፍሪነታቸው በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ላይ ነበር።
18አሁን በውድቀትሽ ቀን የባህር ዳርቻዎችይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕርም ውስጥ ያለ ደሴቶች ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።
19ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፡ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላያትንም ባንቺ ላይ ባስነሳሁብሽ ጊዜ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥
20ያኔ ወደ ጉድጓድ እንደወረዱ ሰዎች ወደ ጥንት ሰዎች አወርድሻለሁ፤ እንደ ጥንት ዘመን ፍርስራሾች በምድር ጥልቅ ውስጥ እንድትኖሪ አደርግሻልችሁ። ከዚህ የተነሳ ሰዎች ወደሚኖሩበት
21ጥፋትን አመጣብሻለሁ ለዘላለምም ትጠፊያለሽ፤ ይፈልጉሻል ነገር ግን ለዘላለም አያገኙሽም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።