መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 25

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አቅንተህ ትንቢት ተናገርባቸው።
3ለአሞንም ሰዎች እንዲህ በል፥ 'የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ "እሰይ!" ብላችኋል።
4ስለዚህ፥ እነሆ፥ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ አሳልፌ አሰጣችኋለሁ፥ እነርሱም በእናንተ ላይ ምሽግን ይሰራሉ ፥ ድንኳኖቻቸውንም በእናንተ ዘንድ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ ወተታችሁንም ይጠጣሉ!
5የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
6ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፥ በእግራችሁም አሸብሽባችኋልና፥ በእስራኤልም ምድር ላይ በነፍሳችሁ ንቀት ሁሉ ደስ ብሏችኋልና
7ስለዚህ፥ እነሆ፥ በእጄን እመታችኋለሁ፥ ለአሕዛብም ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ ከአሕዛብም ለይቼ እቈርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም አጠፋሃለሁ እፈጅህማለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።
8ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ሞዓብና ሴይር እነሆ፥ "የይሁዳ ቤት ያው እንደ ሌሎቹ አሕዛብ ሁሉ ነው!" ብለዋልና
9ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሞዓብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከበኣልሜዎን፥
10ከቂርያታይም፥ ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። የአሞን ህዝብ በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
11በሞዓብም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
12ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ኤዶምያስ በይሁዳ ቤት ላይ በቀል አድርጎአል፥ ይህን በማድረጉም ስህተት ፈጽሟል።
13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ። ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳንም ድረስ ባድማ አደርጋታለሁ፥ በሰይፍም ይወድቃሉ።
14በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ በቀሌንም ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!'
15ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ፍልስጥኤማውያን በንቀት በቀልን አድርገዋልና፥ ይሁዳንም ከውስጣቸው ለማጥፋት ደጋግመው ሞክረዋልና
16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፥ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፥ የባሕሩንም ዳር ቅሬታ አጠፋለሁ።
17በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ በቀሌንም በላያቸው ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።