መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 23

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
2የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።
3በግብጽ አገር በኰረዳነታቸው ዕድሜ አመነዘሩ በዚያ ገለሞቱ። በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸው ጡቶች ተዳበሱ።
4ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የታናሽ እኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ። ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ኦሖላ ሰማርያ ናት ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
5ኦሖላም የእኔ ሆና እያለ ገለሞተችብኝ፤ ውሽሞችዋንም ኃያላኑን ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
6እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ።
7ስለዚህ ራሷን ለተመረጡ ለአሦር ሰዎች ሁሉ ለግልሙትና ሰጠቻቸው ፥ በሴሰኝነት በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።
8በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር።
9ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት።
10እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ በሌሎች ሴቶች ዘንድ መተረቻ ሆነች ስለዚህም ፈረዱባት።
11እኅትዋም ኦሖሊባ ይህን አየች ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በሴሰኝነቷ በረታች፥ ግልሙትናዋም ከእኅትዋ ግልሙትና ይልቅ በዛ።
12አለቆችንና ሹማምቶችን ጎረቤቶችዋን ጌጠኛ ልብስ የለበሱትን በፈረሶች ላይ የሚቀመጡትን ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካሞችን ጐበዛዝት አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
13የረከሰችም እንደ ሆነች አየሁ። የሁለቱም አእህትማማቾች ሁኔታ አንድ ነው።
14ግልሙትናዋንም አበዛች! በቀይ ቀለምም የተሳለውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች።
15በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ! ሁሉም የከለዳዊያን ተወላጆችና የሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።
16ባየቻቸውም ጊዜ ለክፉ ተመኘቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች።
17የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ወደ ሴሰኝነት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች በውርደትም ከእነርሱ ተለየች።
18ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች።
19ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን በማሰላሰል ግልሙትናዋን አበዛች።
20የወንድ ብልቶቻቸው እንደ አህዮች የወንድ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን ውሽሞቿን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው።
21ስለ ኰረዳነትሽ ምክንያት ግብጻውያን ጡቶችሽን የዳበሱበትን ጊዜ የኰረዳነትሽን ሴሰኝነት ተመኘሽ።
22ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'የተለየሻቸውን ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ! ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ!
23እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።
24በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በብዙ ሠራዊትም ይመጡብሻል! ታላላቅና አነስተኛ ጋሻና ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል! እንዲቀጡሽ እድልን እሰጣቸዋለሁ፥ በተግባራቸውም ይቀጡሻል!
25ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ ስለማደርግ በመዓትም ስለሚገናኙሽ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች!
26ልብስሽንም ይገፍፉሻል ጌጣጌጥሽንም ይወስዳሉ!
27አሳፋሪ ባህሪሽን፥ ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስወግዳለሁ። ዓይንሽንም ወደ እነርሱ በናፍቆት አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።
28ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ 'እነሆ፥ በጠላሻቸው እጅ፥ በተለየሻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ!
29እነርሱም በጥላቻ ይገናኙሻል፥ ንብረትሽን ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን ይተዉሻል። የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል።
30ከአሕዛብ ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህ ነገር ይደርስብሻል።
31በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል ስለዚህ የቅጣት ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ።
32ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ!
33በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞያለሽ!
34ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ መጠጫውንም ትሰባብሪዋለሽ በስብርባሪውም ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፦
35ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ረስተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ የሴሰኝነትሽንና የግልሙትናሽን ውጤት ተሸከሚ።
36እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ አሳፋሪ ተግባራቸውን አስታውቃቸው
37አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና! ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን ለእሳት መቃጠል አሳልፈዋቸዋልና።
38ይህን በእኔ ላይ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል!
39ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉበት በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ! እነሆም፥ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት ይህ ነው።
40ደግሞ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች መልእክተኛ ልከሻቸዋል። እነርሱም መጥተዋል! እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽና ዓይኖችሽን ትኩለሽ አጊጠሽም ጠብቅሻቸው።
41ከፊት ለፊቱ ገብታ በተዘጋጀበት በክብር አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም አኖርሽበት።
42በጭንቀት የተሞላ የህዝብ ድምፅ በአንቺ ዘንድ ነበረ፥ ሰካራሞችም ከሌሎች ምናምንቴ ሰዎች ጋር ከምድረ በዳ መጡ። በእጅሽም ላይ አንባር በራስሽም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉ።
43እኔም በምንዝር ስለሻገተችው ፥ 'አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች' አልሁ።'
44ወደ ጋለሞታም እንደሚገቡ ወደ እርስዋ ገቡ እንዲሁ ይሴስኑ ዘንድ በግልሙትና በደለኛ ወደሆኑት ወደ ኦሖላና ወደ ኦሖሊባ ገቡ።
45ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች ለአመንዝሮቹና ለደም አፍሳሾቹ የተመደበውን ቅጣት ያስተላልፉባቸዋል።
46ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ጦር አመጣባቸዋለሁ፥ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ አሰጣቸዋለሁ።
47ሠራዊቱም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።
48ከእንግዲህ ሴቶች ሁሉ የሴሰኝነት ተግባር እንዳይፈጽሙ ሴሰኝነትን ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ።
49ሴሰኝነታችሁንም በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ። እናንተም ኃጢአታችሁንና ጣዖቶቻችሁን ትሸከማላችሁ በዚህ መንገድ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።