መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
2"አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።
3እንዲህም ልትላት ይገባል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ይህች ጊዜዋ እንዲደርስ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ፤ እንድትረክስም ጣዖታትን የምታደርግ ከተማ ናት!
4ስላፈሰስሽው ደም በደለኛ ነሽ ፥ ባደረግሽውም ጣዖታት ረክሰሻል! ቀንሽን አቀረብሽ ዘመንሽንም አሳጠርሽ። ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደርግሻለሁ።
5አንቺ ስምሽ የረከሰ ግራ መጋባት የሞላብሽ ሆይ፥ በቅርብም በሩቅም ያሉ ይሳለቁብሻል።
6እነሆ፥ የእስራኤል አለቆች እያንዳንዳቸው በኃይላቸው መጠን ደም ያፈስሱ ዘንድ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።
7በውስጥሽ አባቶችንና እናቶችም አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ። በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።
8ቅዱሳቴንም ናቅሽ ሰንበታቴንም አረከስሽ!
9ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ በተራሮችም ላይ በሉ። በመካከልሽ ክፋትን አደረጉ።
10በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ኀፍረተ ሥጋ ገለጡ በአንቺም ውስጥ በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት አዋረዱ።
11በባልንጀራቸው ሚስቶች ጋር ርኵሰትን ያደርጉ፥ የልጆቻአውን ሚስቶች ያረከሱ፥ የገዛ አባቶቻቸውን ሴት ልጆች እህቶቻችውን ያስነወሩ፥ እንዲህ ያሉ ስዎች ሁሉ በአንቺ ውስጥ አሉ።
12በአንቺ ውስጥ ደምን ለማፍሰስ ጉቦን ይቀብላሉ። አንቺም አራጣና አላስፈላጊ ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽን በጭቆና ጎዳሻቸው ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
13ስለዚህ፥ እነሆ፥ ያለቅንነት የሰበሰብሽውን ሀብት በመካከልሽ ያለውን ደም ማፍስስ በእጄ እቀጣለሁ።
14በውኑ እኔ ይህን በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ።
15ወደ አሕዛብም እበትንሻለሁ ወደ አገሮችም እዘራሻለሁ። በዚህ መንገድ ርኵሰትሽን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።
16በአሕዛብም ፊት አንቺ የረከሽ ትሆኚያለሽ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂአለሽ።
17ቀጥሎም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
18የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ለእኔ እንደ ዝቃጭ ሆኑብኝ። እነርሱ ሁሉ በእንቺ ውስጥ የመዳብና የቆርቆሮ ፥ የብረትና የእርሳስ ተረፍ ምርት ናቸው። እነርሱ በማቅለጫ ውስጥ የብር ዝቃጭ ናቸው።
19ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ዝቃጭ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ።
20እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ አቀልጣችኋለሁ። ስለዚህ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ እሳትም አናፋባችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።
21ስለዚህም አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።
22ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጧ ትቀልጣላችሁ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።
23የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
24የሰው ልጅ ሆይ እንዲህ በላት 'አንቺ ያልነጻሽ ምድር ነሽ። በቍጣ ቀን ዝናብ የለም!
25በውስጥዋ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና እንደሚናጠቅ አንበሳ አንድ ሆነው ተማምለው ህይወት ያጠፋሉ፥ ከፍ ያለ ብልጥግና ይወስዳሉ! በውስጥዋም መበለቶችን ያበዛሉ!
26ካህናቶችዋም ሕጌን አቃለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል። ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አይለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አያስተምሩም። ፊታቸውንም ከሰንበታቴ መለሱ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
27በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው። የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈሳሉ ህይወትንም ያጠፋሉ።
28እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።
29የምድሪቱም ሕዝብ በማስፈራራት ግፍ አደረጉ ዘረፋ ፈጸሙ፥ ድሆችንና ችግረኞችን አስጨነቁ፥ ያለ ፍትህ መጻተኛውንም በደሉ።
30ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አንድም ሰው አላገኘሁም።
31ስለዚህ ቍጣዬን አፈስባቸዋልሁ፥ በመዓቴም እሳት አጠፋቸዋለሁ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።