1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና በመቅደሶችም ላይ ተናገር፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።
3ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውንም ከእናንተ ዘንድ አጠፋለሁ።
4እኔም ጻድቁንና ክፉውን ከእናንተ ዘንድ ስለማጠፋ፥ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ባለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።
5ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ ስይፌም ከእንግዲህ አይመለስም!
6ስለዚህም፥ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አልቅስ ወገብህን በማጕበጥ በፊታቸው ምርር ብለህ አልቅስ።
7እነርሱም 'ስለ ምን ታለቅሳለህ?' ብለው ይጠይቁሀል፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ 'ስለሚምጣው ክፉ ዜና ነው፥ ምክንያቱም ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስም ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበትም እንደ ውኃ ይፈስሳል። እነሆ፥ ይመጣል ይፈጸምማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር'"
8የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
9የሰው ልጅ ሆይ፥ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር ሰይፍ! ሰይፍ! የተሳለና የተወለወለ ሰይፍ በል።
10ለታላቅ ግድያ ተስሎአል! እንደመብረቅም እንዲያብረቀርቅ ይወለወላል! በልጄን በትረ መንግስት ደስ ሊለን ይገባልን? የሚመጣው ስይፍ የዚህ አይነቱን በትር ይጠላል።
11ሰይፉም እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ይሰጣል! ሰይፉ የትሳል ነው! ለገዳይም ሊስጥ ተወልውሎ ተዘጋጅቷል!'
12የሰው ልጅ ሆይ፥ ሰይፉ እየመጣ ያለው በሕዝቤ ላይ ነውና፥ ለሰይፉም የሚሰጡት የእስራኤል አለቆች ሁሉ ናቸውና ለእርዳታ ተጣራ፥ አልቅስ! ሕዝቤ ነበሩና ስለዚህ ጭንህን በምሬት ጽፋ!
13ፈተና ደርሶአል፥ በትረ መንግስት ቢጸና ምን ዋጋ አለው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
14ስለዚህ፥ አንተ የሰው ልጅ፥ ትንቢት ተናገር፥ እጅህን አጨብጭብ ሰይፍ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃት ይፈጽማልና! ለሚታረዱ የተዘጋጅ ስይፍ! ሰውነታቸውን ሁሉ ሊወጋ ለሚታረዱ ለብዙዎች ሰዎች የተመደበ ሰይፍ ነው!
15ልባቸው እንዲቀልጥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ! ወዮ! እንድመብረቅ ሆኗል እንዲገድልም ነጻ ተለቋል።
16ሰይፍ ሆይ ተዘጋጅ! ስለትህ ወደፈቀደው ወደ ቅኝም ወደ ግራም ምታ።
17እኔ ደግሞ በእጄ አጨበጭባለሁ መዓቴንም እፈጽማለሁ! እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።"
18የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥
19"አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣ ዘንድ ሁለት መንገዶችን አድርግ። ሁለቱም መንገዶች ከአንድ ምድር ይነሳሉ፥ የመንገድ ምልክቱም አንደኛው መንገድ ወደ ከተማ እንድሚወስድ ያሳያል።
20አንዱ መንገድ የባቢሎን ጦር ወደ አሞናዊያን ከተማ ወድ ረባት እንድሚወስድ አመልክት። ሌላኛው መንገድ ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንድሚወስድ አመልክት።
21የባቢሎን ንጉሥ የጥንቆላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ መታጠፊያ ላይ ይቆማል። ፍላጾችን ይወዘውዛል፥ ከጣዖታቱም ምሪት ይጠይቃል። ጉበትም ይመለከታል።
22የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።
23በኢየሩሳሌም ላሉ ለባቢሎናዊያን መሐላን ማሉ ዓይን ፊት የሐሰት ምዋርት ይመስላል፥ ነገር ግን ንጉሱ እንዲያዙ ለማድረግ ስምምነታችሁን አፍርሳችኋል ብሎ ይከሳቸዋል።
24ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን እንዳስብ ስላደርጋችሁኝ መተላለፋችሁ ይገለጣል! ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ይታያል! በዚህም ምክንያት በጠላቶቻችሁ እጅ እንደተያዛችሁ ስውን ሁሉ ታሳስባላችሁ!
25አንተም የምትቀጣበት ቀን የደረስብህ ፥ አመጻ የማድረጊያ ዘመን ያበቃብህ፥ አመጸኛና ክፉ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥
26ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም ከራስህ ላይ አንሳ! ከእንግዲ ነገሮች እንደነበሩ አይቀጥሉም! የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ።
27ባድማ፥ ባድማ፥ ሁሉንም ባድማ አደርጋለሁ! የሚገባው ሰው እስኪመጣና ለእርሱ እስከምሰጠው ድረስ ንግስና ከእንግዲህ አይኖርም።
28አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለሚመጣባቸው ውርደት ለአሞን ልጆች እንዲህ ይላል፡ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዟል! ለማጥፋትና ለመግደል ተስሏል፤ እንደመብረቅም ያብለጨልጫል!
29ነቢያት ባዶ ራዕይ እያዩልህና ምዋርት እያሟረቱልህ ሳለ ይህ ሰይፍ ሊገደሉ ባሉት የሚቀጡበት ቀን በደረሰባቸው የእመጽ ዘመናቸው ባበቃባቸው ሰዎች አንገት ላይ ያርፋል።
30ሰይፉን ወደ ሰገባውም መልሰው። በተፈጠርህበት ስፍራ በተወለድህባትም ምድር እፈርድብሃለሁ!
31ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ! የመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፥ በማጥፋት ለተካኑ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ!
32ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ! ደምህም በምድሪቱ መካከል ይፈሳል፥ መታሰቢያም አይኖርህም፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።