መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰላሳኛው ዓመት ክአመቱም በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬብሮን አጠገብ ከምርኮኞቹ ጋር አብሬ እየኖርኩኝ ሳለሁ ሰማያት ተክፍተው የእግዚአብሔርን ራዕይ አየሁ።
2ንጉስ ኢዮአኬም በተማረከበት በአምስተኛው ቀን በከለዳዊያን አገር በኬብሮን ወንዝ አጠገብ
3የእግዚአብሔር ቃል ወደ ካህኑ ወደ ኡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል በኃይል መጣ። የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች።
4እኔም በውስጡ የእሳት ነበልባል ያለበት ዙሪያውና ውስጡ የሚያበራ ታላቅ ደመና የሚመስል አውሎ ነፋስ ከሰሜን አቅጣጫ ሲመጣ አየሁ፣ በደመናው ውስጥ ያለው እሳት ቀለሙ ቢጫ ነበር።
5መካከል ላይ የአራት ህያዋን ፍጡራን ምስል ነበር። ፍጥረታቱ የሰው መልክ ነበራቸው፣
6ነገር ግን እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊቶችና አራት አራት ክንፎች ነበሩዋቸው።
7እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፣ ነገር ግን የእግሮቻችው ኮቴ እንደ ነሀስ የሚያበራ የጥጃ ኮቴ ያለ ነበር።
8ከክንፎቻቸው ስር በአራቱም አቅጣጫ የሰው እጅ ነበራቸው።
9በክንፎቻቸው ተነካክተው ወደ ኋላ ሳይገላመጡ ቀጥ ብለው ወደፊት ይራመዱ ነበር።
10መልካቸውም በአንድ በኩል የሰው፥ በቀኝ በኩል የአንበሳ፣ በግራ በኩል የበሬና በሌላ በኩል ደግሞ የንስር ነበር።
11መልካቸው ያንን ይመስል ነበር፣ ክንፎቻቸውም ተዘርግተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተነካክተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።
12እያንዳንዳቸው ሳይገላመጡ ወደፊት ይራመዱ ነበር፣ መንፈስ ወደመራቸው ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
13ህያዋን ፍጡራን የከሰል ፍም እሳት ወይም ችቦ ይመስሉ ነበር፣ ከህያዋን ፍጡራኑ ጋር ደማቅ እሳት ይንቀሳቀስ ነበር፣ የመብረቅ ብልጭታዎችም ነበሩ።
14ህያዋን ፍጡራኑ በዝግታ ወደ ኋላና ወደ ፊት ይንቀሳቀሱ ነበር፣ እንደ መብረቅም ነበሩ።
15ወዲያውም ወደ ህያዋን ፍጥረታቱ ተመለከትኩ፣ በምድር ላይ ከእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኮራኩር ነበረ።
16የመንኮራኩረቹ መልክ የሚከተለውን ይመስል ነበር፡ እንደ ብርሌ ያንጸባርቁ ነበር፣ አራቱም አንድ አይነት ነበሩ፣ አንዱም በአንዱ ላይ የተስካ ይመስል ነበር።
17መንኮራኩሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ፍጡራኑ ወደየትኛውም አቅጣጫ ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
18ዙሪያውን በዓይን የተሞላ ስለሆነ የመንኮራኩሮቹ ጠርዝ ርጅምና አስፈሪ ነበር።
19ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንኮራኩሮቹ አብረው ይንቀሳቀሱ ነበር፣ ህያዋን ፍጥረታቱ ወደ ላይ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ይሉ ነበር።
20መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዱ ነበር፣ የህያዋን ፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው መንኮራኩሮቹ አብረው ወደ ላይ ከፍ ይሉ ነበር።
21የፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው ፍጡራኑ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም ከአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፣ ሲቆሙ እነርሱም ይቆሙ ነበር፣ ከምድር ወደ ላይ ከፍ ሲሉ እነርሱም ከፍ ይሉ ነበር።
22ከህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ ጠፈር የሚምስል ነገር ነበረ፤ ያም ጠፈር የሚመስል ነገር በህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ እንደ አስፈሪ በረዶ ዙሪያቸውን ነበረ።
23ከጠፈሩ በታች የእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ክንፍ ቀጥ ብሎ ተዘርግቶ የአንደኛው ፍጡር ክንፍ ከሌላው ፍጡር ክንፍ ጋር ተነካክቶ ነበር። እያንዳምዱ ፍጡር ሰውነቱን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፍ ነበረው።
24ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሁሉ የክንፎቻቸው ድምጽ ይሰማኝ ነበር፣ ድምጹም እንደ ውሃ ጎርፍ፣እንደ ህያው አምላክ ድምጽ፣ እንደ ሠራዊት ድምጽ፣ እንደ ዝናብ ውሽንፍር ነበረ! በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻችውን ያጥፉ ነበር።
25በሚቆሙበትና ክንፎቻቸውን በሚያጥፉበት ጊዜ ከራሶቻቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምጽ ይመጣ ነበር።
26ከራሶቻቸው በላይ ከሚገኘው ጠፈር በላይ ዕንቁ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበር፣ በዙፋኑም አምሳያ ላይ ሰው የሚመስል ተቀምጦ ነበር።
27ከወገብ በላይ በእሳት የጋለ ብረት ከወገቡ በታች ደግሞ እሳት የሚመስል ምስል አየሁ።
28በዝናብ ጊዜ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ይመስል ዙሪያውም ደማቅ ብርሀን ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፣ ወዲያውም የሚያናግረኝ ድምጽ ሰማሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።