1አንተም በእስራኤል አለቆች ላይ ይህን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በል፥
2'እናትህ ማን ነበረች? አንበሳ ነበረች ከአንበሳ ደቦል ጋር ተጋደመች ግልገሎችዋን አሳደገች።
3ከግልገሎችዋም አንዱን ደቦል አንበሳ እንዲሆንና ጠላቶቹን የሚቆራርጥ እንዲሆን አሳደገችው። ሰዎችንም በላ።
4አሕዛብም ወሬውን ሰሙ እርሱም በወጥመዳቸው ተያዘ፥ በሰንሰለትም አድርገው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።
5እርስዋም ይመለሳል ብላ ብትጠብቅም ተስፋዋ እንደ ጠፋ ባየች ጊዜ፥ ከግልገሎችዋ ሌላን ወስዳ ደቦል አንበሳ እንዲሆን አሳደገችው።
6ደቦል አንበሳውም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ ደቦል አንበሳም ሆነ ንጥቂያም ተማረ፥ ሰዎችንም በላ።
7መበለቶቻቸውን አስነወረ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረሰ ከግሣቱም ድምፅ የተነሣ ምድሪቱና በሞላ ሰው አልባ ሆነች።
8አሕዛብም ከየአገሩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ መረባቸውንም በእርሱ ላይ ዘረጉ በወጥመዳቸውም ተያዘ።
9በሰንሰለትም አድርገው በሳጥን አድርገው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ አምባ አመጡት።
10እናትህ በውኃ አጠገብ በደምህ ውስጥ እንደ ተተከለች ወይን ነበረች። ከውኃም ብዛት የተነሣ ፍሬያማና በቅርንጫፍ የትሞላች ነበረች ።
11ለእርስዋም ብርቱዎች በትሮች ነበሩአት እነርሱም ለነገሥታት በትሮች ነበሩ። ቁመቷም በዛፎች ቅርንጫፎች መካከል ከፍ አለ።
12ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስም ፍሬዋን አደረቀ። ብርቱዎች ቅርንጫፎቿተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻው።
13አሁን በምድረ በዳ፥ በደረቅና ውሀ በሌለው መሬት ተተክላለች።
14ከቅርንጫፎቿ እሳት ወጥቶ ፍሬዋ በላ፥ ጠንካራ ቅርንጫፍ የለባትም የነገሥታትም በትር ሊሆን የሚችልም የለም።' ይህ ሙሾ ነው፥ የልቅሶ ዝማሬም ይሆናል።