መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ የወይን ግንድ፥ በዱር ዛፎች መካከል ካለ ቅርንጫፎቼ ካሉት ማንኛውም ዛፍ ብልጫው ምንድር ነው?
3በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከወይን ግንድ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ችካል ከእርሱ ይወስዳሉን?
4እነሆ፥ ለመቃጠል በእሳት ላይ ቢጣል ፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹንና በልቶአል፥ መካከሉንም ቢያቃጥለው በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?
5እነሆ፥ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላው እርሱም ከተቃጠለ በኋላ ለምንም አይጠቅምም!
6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ካሉት ዛፎች ይልቅ የወይን ግንዱን እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።
7ፊቴንም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ ከእሳትም ይወጣሉ፥ እሳት ግን ይበላቸዋል ፊቴንም በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
8ዓመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።