መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእስራኤልም ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።
2ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
3የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል የበደላቸውንም መቅሠፍት በፊታቸው አቁመዋል ታዲያ እኔ ከእነርሱ ጥያቄ መቀበል አለብኝ?
4ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።
5ይህንንም የማደርገው ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት ከእኔ በጣም በራቀው በልባቸው የእስራኤልን ቤት እንደገና ለመመለስ ነው!' ብለህ ንገራቸው።
6ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ፊታችሁንም ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ።
7ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች ማንም፥ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ ያኖረ፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ ያቆም ሰው ሁሉ፥ ጥያቄ ይዞ ወደ ነቢዩ ቢመጣ ፥ እኔ እግዚአብሔር እራሴ እመልስለታለሁ!
8ፊቴንም እዞርበታለሁ ከሕዝቤም መካከል አጠፋውና መቀጣጫና ምሳሌም አደርገዋለሁ ፣ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!
9ነቢዩም ስቶ ሳለ መልዕክትን ቢናገር፥ እኔ እግዚአብሔር ያንን ነቢይ አስተዋለሁ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።
10ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ የነቢዩ ኃጢአት መልዕክት ፍለጋ ወደእርሱ የሄደ ሰው ኃጢአት አንድ ይሆናል።
11በዚህም ምክንያት ከዚህ በኋላ የእስራኤል ቤት ከእኔ ርቀው አይቅበዘበዙም በኃጢአታቸውም ሁሉ አይረክሱም። እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
12የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
13የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር በማመፅ በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እኔም እጄን ብዘረጋባት የእንጀራዋንም በትር ብሰብር ራብን ብሰድድባት ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥
14እነዚህም ሦስት ሰዎች፥ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብም፥ በመካከልዋ ቢገኙ እነርሱ በጽድቃቸው ሊያዱኑ የሚችሉት የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ነበር፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
15ክፉዎቹን አራዊት በምድር ባሳልፍ እነርሱም ልጆችዋን ቢያጠፉ ስለ አራዊትም ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥
16እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
17ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ። ሰይፍ ሆይ፥ በምድሪቱ ላይ እለፊ ብል፥ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥
18እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
19ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ለማጥፋት መዓቴን በደም ባፈስስባት፥
20ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
21ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ በመስደድ ነገሮች እንዲከፉ አደርጋለሁ።
22ነገር ግን፥ እነሆ! ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ጋር የሚያመልጡ ቅሬታዎች ይተርፉላታል። እነሆ! ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ቅጣት በምድሪቱም ላይ ስላመጣሁባት ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ ።
23መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።