መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን 'የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!
3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንምን ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉ ለሰነፎች ነቢያት ወዮላቸው!
4እስራኤል ሆይ፥ ነቢያትህ በምድረ በዳ እንደሚኖሩ ቀበሮች ናቸው።
5፥ በእግዚአብሔርም ቀን በሰልፍ ትቆሙ ዘንድ ልትጠግኑት ወደ ፈረሰው ቅጥር አልወጣችሁም ።
6እግዚአብሔር ሳይልካቸው "እግዚአብሔር እንዲህና እንዲህ ይላል" የሚሉ ሰዎች ውሸተኛ ትንቢትንና ውሸተኛ ራዕይን አይተዋል። ያም ሆኖ ግን ቃላቸው እንደሚፈጸም ተስፋ ያደርጋሉ።
7እኔም ሳልናገር "እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል" የምትሉ እናንተ ከንቱ ራእይን ያያችሁ ውሸተኛንም ትንቢትን መናገራቼሁ አይደለምን?
8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ ውሸት ስለተናገራችሁ ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረው ይህ ነው፡
9እጄም ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ የውሸት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ይሆናል። እነርሱም በሕዝቤ ጉባኤ ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤልም ቤት መዝገብ ላይ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!
10በዚህም ምክንያት ሰላም ሳይኖር "ሰላም ነው!" እያሉ ሕዝቤን መረን ሰደዋል፣ ገለባ በሌለበት ጭቃ የተመረገ ቅጥር ይገነባሉ።
11ቅጥሩን ገለባ በሌለበት ጭቃ ለሚመርጉት ሰዎች እንዲህ በላቸው 'ቅጥሩ ይወድቃል፤ የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፥ ቅጥሩኔ ለማፍረስ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ እልካለሁ፥ እንዲያደቀውም ዐውሎ ነፋስን እልካለሁ።
12እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ። የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን?
13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'በመዓቴ ዐውሎ ነፋስ አመጣለሁ ፥ በቍጣዬም ዶፍ ዝናብ ይዘንባል! በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ፈጽሞ ያወድመዋል።
14ገለባም በሌለበት ጭቃ የመረጋችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይናዳል እናንተም በመካከሉ ትጠፋላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
15በመዓቴም ግንቡንና ገለባ በሌለው ጭቃ የመረጉትን ሰዎችአጠፋለሁ። ግንቡም ሆነ መራጊዎቹ የሉም እላችኋለሁ።
16እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩ የሰላምን ራእይ የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው። ሰላምም የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"
17አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ከገዛ ልባቸው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ ትንቢትም ተናገርባቸው፥
18እንዲህም በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ በመላ እጆቸው የጥንቆላ መከዳ ለሚሰፉ ለራሶቻቸውም የተለያየ መጠን ያላቸው ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?
19ውሸታችሁን ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ ለጭብጥ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ብላችሁ መሞት የማይገባቸውን ለመግደል በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን በሕይወት በማኖር በሕዝቤ ፊትአርክሳችሁኛል።
20ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በአስማት መተቶቻችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀደዋለሁ፥ እንደ ወፍም ያጠመዳችኋቸውን ህዝብ ነጻ አወጣለሁ።
21ሽፋኖቻችሁንም እቀድዳለሁ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚያም ወዲያ በእጃችሁ አይጠመዱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
22እኔም እንዲያዝን የማልፈልገውን የጻድቁን ልብ በውሸታችሁ አሳዝናችኋልና፥ በተቃራኒው ደግሞ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር የኃጢአተኛውን ተግባር አበረታታችኋልና
23ሕዝቤን ከእጃችሁ ስለማድን ክእንግዲህ ከንቱን ራእይ አታዩም የውሸት ትንቢትም አትናገሩም፥ ምክንያቱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።