1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
2"የሰው ልጅ ሆይ፥ የምትኖረውዓመጸኞች ከመሆናቸው የተነሳ አይን እያላቸው በማያዩ ጆሮ እያላቸው በማይሰሙ በዓመፀኛ ሰዎች መካከል ነው!
3አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ ለስደት ተዘጋጅ ምክንያቱም በፊታቸውም በጠራራ ፀሀይ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ተማርከህ እንድትሄድ አደርጋለ። ምናልባት ይህን ሲያዩ ዓመፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ያስተውሉ ይሆናል።
4እቃዎችህን ሰብስበህ በቀን በፊታቸው ለስደት ተዘጋጅ፤ በማታም ጊዜ በፊታቸው ልክ ስደተኞች እንደሚያደርጉት ሂድ።
5እያዩህም ግንቡን ፈንቅለውና በእዚያ በኩል ውጣ።
6እያዩህም እቃዎችህን በጫንቃህ ላይ ተሸከምና በጨለማ ውጣ። ለእስራኤልም ህዝብ ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።
7እንዳዘዘኝም አደረግሁ። በቀንም የስደት እቃዬን ወስጄ ማታ ላይ ግንቡን በእጄ ፈነቀልኩና በጨለማ አወጣቼ እያዩኝ በጫንቃዬ ላይ ተሸከምሁት።
8በነጋታውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
9"የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓመፀኛው የእስራኤል ቤት 'የምታደርገው ምንድር ነው?' ብለው ጠየቁህን?
10አንተም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ይህ ትንቢታዊ ጉዳይ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን አለቃና በመካከላቸውም የሚኖሩትን የእስራኤል ቤትን ሁሉ የሚመለከት ነው' በላቸው።
11ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም በስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ በላቸው።
12በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ ንብረቱን በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ግንቡን ፈንቅሎ በጨለማ ይወጣል። ንብረታቸውን ለማውጣት ግንቡን ይፈነቅላሉ። አለቃውም በዓይኑ ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።
13መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።
14ሊረዱትም በዙሪያው ያሉትን ሁሉና ወታደሮቹን ሁሉ በየእቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፣ከኋላቸውም ሰይፍ እልክባቸዋለሁ።
15በአሕዛብም መካከል በበተንኋቸው ጊዜ፥ በአገሮችም በዘራኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
16ነገር ግን በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ እንዲመዘግቡ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አተርፋለሁ፣ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
17የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
18"የሰው ልጅ ሆይ፥ እንጀራህን በመረበሽ ብላ ውኃህንም በመንቀጥቀጥና በኀዘን ጠጣ።
19ለምድሪቱም ሕዝብ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ ይላል 'ክሚኖሩባት ሰዎች አመጽ የተንሳ ምድሪቱ ሞላዋ ስለምትጠፋ እንጀራቸውን በመረበሽ ወኃቸውንም በድንጋጤ ይጠጣሉ።
20ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ባድማ ይሆናሉ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።
21የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ,
22"የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር የሚነገረው'ዘመኑ ረዝሞአል ራእዩም ሁሉ ጠፍቶአል' የሚለው ምሳሌ ምንድር ነው?
23ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ክዚህ በኋላ የእስራኤል ህዝብ እንዳይጠቀሙበት ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ ።' ከዚያም እንዲህ በላቸው "ዘመኑ ቀርቦአል እያንዳንዱ ራዕይም ይናገራል!'
24ምክንያቱም ከዚህ በኋላ በእስራኤል ቤት መካከል ከንቱ ራእይና ውሸተኛ ምዋርት አይሆንም።
25እኔ እግዚአብሔር ነኝና! እናገራለሁ የተናገርኩትንም ቃል እፈጽማለሁ። ነገሩ ከእንግዲህ አይዘገይም። እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
26የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል እንደገና መጣ፣
27"የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የእስራኤል ቤት 'ይህ ያየው ራእይ ገና ስለወደፊቱ ነው ስለሩቅ ዘመንም ትንቢት ይናገራል' ብለዋል።
28ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከዚህ በኋላ አይዘገይም' ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው!"