መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሕዝቅኤል 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1መንፈስም አነሣኝ ወደ ምስራቅ መውጫ ወደሚመለከት ወደ እግዚአብሔር ቤት ምሥራቅ በር አመጣኝ። እነሆም፥ በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስ ልጅ ፈላጥያን አየሁ።
2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያስቡ በዚህችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው።
3እነርሱም 'ቤቶችን የምንሠራበት ዘመን አይደለም። ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን' ብለዋል።
4ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገርባቸው፣ ትንቢት ተናገር።
5የእግዚአብሔርም መንፈስ በኔ ላይ ሆኖ እንዲህ አለኝ፥ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔም የልባችሁን አሳብ አውቃለሁ።
6በዚህች ከተማ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ገድላችኋል ጎዳናዎችዋንም በሬሳዎቻቸው ሞልታችኋል።
7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአየሩሳሌም ከተማ መካከልም ሬሳዎቻቸው ያኖራችኋቸው የገደላቹኋቸው ሰዎች ሥጋው ሲሆኑ፥ ይህችም ከተማ ድስቱ ናት። እናንተን ግን ከከተማዋ መካከል ተነቅላችሁ ትወጣላችሁ።
8ሰይፍን ፈርታችኋል እኔም ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
9ከከተማይቱ መካከል አወጣችኋለሁ፥ በእንግዶችም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ በላያችሁም ፍርድ አመጣባችኋለሁ።
10በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
11ይህች ከተማ የማብሰያ ድስት አትሆንላችሁም እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፣ እኔም በእስራኤል ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ።
12እኔም በትዕዛዙ ያልሄዳችሁለት ፍርዱንም ያላደረግችሁለት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። ይልቁኑ በዙሪያችሁ እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።
13እንዲህም ሆነ ትንቢትም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፣ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?" ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።
14የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ
15"የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ! አዎ ወንድሞችህ! ዘመዶችህ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ! 'እነርሱ ከእግዚአብሔር የራቁ ናቸው! ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች' የሚሉአቸው ናቸው።
16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፣ 'ምንም እንኳ እኔ በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ ባርቃቸውና ወደ አገሮችም ብበትናቸውም በሄዱባቸው አገሮች ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስ ሆኜላቸዋለሁ' ።
17ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው 'ከአሕዛብ ዘንድ አከማቻችኋለሁ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።
18ወደዚያም ይመጣሉ፥ ጸያፉንና ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከዚያች ምድር ያስወግዳሉ።
19ወደኔ ሲቀርቡ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አስቀምጣለሁ፤
20ከሥጋቸውም ውስጥ ድንጋዩን ልብ አውጥቼ የሥጋን ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ ይህም በትእዛዜም እንዲሄዱና ፍርዴንም እንዲጠብቁና እንዲያደርጉት ነው። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
21በልባቸው ወደ ጸያፍና ርኩስ ነገሮቻቸው በሚሄዱት ላይ መንገዳቸውን ወደራሳቸው እመልሳለሁ። ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው። "
22ኪሩቤልም ክንፎቻቸውንና በአጠገባቸው የነበሩትን መንኰራኵሮች ከፍ አደረጉ፣ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።
23የእግዚአብሔርም ክብር ከከተማይቱ ውስጥ ተነሥቶ በከተማይቱ ምሥራቅ በኩል ባለው ተራራ ላይ ቆመ።
24መንፈስም አነሣኝ፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ በሆነ ራእይ ምርኮኞቹ ወዳሉበት ወደ ከላውዴዎን ምድር አመጣኝ። ያየሁትም ራእይ ከእኔ ተለየ።
25ከዚያም እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞች ነገርኳቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።